ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የህትመት ውጤቶች፣ የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞች (ቶነሮች)፣ የሰራተኞች ደንብ ልብስ እና የፅዳት ዕቃዎች መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የህትመት ውጤቶች፣ የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞች (ቶነሮች)፣ የሰራተኞች ደንብ ልብስ እና የፅዳት ዕቃዎች ከዚህ በታች በቀረቡት ምድብ መሰረት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ምድብ አንድ፡- የፅህፈት መሳሪያዎች
  • ምድብ ሁለት፡- የህትመት ውጤቶች
  • ምድብ ሦስት፡ የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞች(ቶነሮች)
  • ምድብ አራት፡- የሰራተኞች ደንብ ልብስ
  • ምድብ አምስት፡- የፅዳት እቃዎች

በዚሁም መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ::

1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ ለሚፈልጉት ምድብ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው እስከሚያበቃበት ቀን ድረስ በኩባንያው ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ስራ አስፈፃሚ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

3. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. በብርሃን  ኢንሹራንስ ኢማ ስም አዘጋጅቶ ማስያዝ ይኖርበታል።

4. ጨረታ ሰነዱን በፓስታ አሽጎ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በአካል ተገኝተው ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ማንኛውም ተጫራች ለመጫረት ለተወዳደረበት የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የህትመት ውጤቶች፣ የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞች (ቶነሮች)፣ የሰራተኞች ደንብ ልብስ እና የፅዳት ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል።

6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያጠቃልል መሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው ሀምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

8. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ
ብርሃን ኢንሹራንስ ኢማ ዋናው መ/ቤት
ወሎ ሰፈር ጋራድ ህንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7 የሠው ሀብትና ንብረት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ ስልክ 011 467 4423/46 ወይም 011 470 4054


Tender details

  • Deadline: 2026-07-15
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-07-15 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Berhan Insurance S.C.
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Jun 28, 2026
  • Posted at: 2026-06-30T06:55:48.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders