መድን ፋና ትራንስፖርት ሎጂስቲክስና ንግድ አ.ማ. የተለያዩ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ቁርጥራጭ ብረቶች፣ ጎማዎች፣ የተቃጠለ ዘይትና ጀሪካን በጨረታ በማወዳደር ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሉ ዕቃዎች ጨረታ

አክስዮን ማህበራችን መድን ፋና ትራንስፖርት ሎጂስቲክስና ንግድ አ.ማ የተለያዩ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ቁርጥራጭ ብረቶች፣ ጎማዎች፣ የተቃጠለ ዘይትና ጀሪካን በጨረታ በማወዳደር ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።

1. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ዋናው መስሪያ ቤት በሚገኝበት ጎተራ ማሳለጫ ከአቦኝ ህንጻ አጠገብ በመገኘት ከቢሮ ቁጥር 13 የማይመለስ ብር ሦስት መቶ በመክፈል መውሰድ ይችላ።

2. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የተቀመጠውን የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሰረት ከብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) እስከ ብር 10,000 (አስር ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በአክስዮን ማህበሩ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውንና የሚወዳደሩበትን ሎት በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኤምቨሎፕ እስከ ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ጨረታው መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ላይ ታሽጎ በእለቱ 8፡30 ላይ ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡-

  • ተጫራቾች ዕቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በአካል ተገኝተው ማየት ይችላሉ።
  • አክስዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ

በመደበኛ ስልክ ቁጥር: 011 470 8186

በተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥር: 09 13-30 07 14 መደወል ይችላሉ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-06
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-07-06 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: መድን ፋና ትራንስፖርት ሎጂስቲክስና ንግድ አ.ማ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jun 28, 2026
  • Posted at: 2026-06-30T11:26:34.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders