የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የመኖሪያ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ አውጥቷል
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በአፈፃፀም ከሳሽ አቶ ኤሊያስ ሞጆ እና በአፈፃፀም ተከሳሽ አቶ ብርሃኑ ታደሰ ሻመሮ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ በሀዋሳ ከተማ መናኸሪያ ክ/ከተማ ሚሊኒየም ቀበሌ ውስጥ በአፈፃፀም ተከሳሽ አቶ ብርሃኑ ታደሰ ሻመሮ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የቦታ መለያ ቁጥር SN001010608125 የቦታ ስፋት 350.75 ካሬ ሜትር የመኖሪያ ቤት ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የመና/ክ/ከ/ልማትና ኮ/ን/ጽ/ቤት በላኩት መነሻግምት ዋጋ ብር 9,977,497.44 (ዘጠኝሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰባ ሰባት ሺህ አራት መቶ ዘጠና ሰባት ብር ከአርባ አራት ሳንቲም) ሆኖ በሐራጅ እንዲሸጥ እና የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ 24/10/2018ዓ/ም ጀምሮ እስከ 24/11/2018ዓ/ም ለ30 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ የሀራጅ ሽያጩ በ25/11/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ በሐራጅ እንዲሸጥ ተወስኗል።
ስለሆነም፦
- በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች/ ሕጋዊ ወኪሎች ለጨረታው ማስከበሪያ የመነሻ ዋጋውን 1/4ኛ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ተኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 030 በአካል ቀርባችሁ በማስያዝ እና ያስያዛችሁበትን ሕጋዊ ደረሰኝ ይዛችሁ በመቅረብ ጨረታውን መሳተፍ ትችላላችሁ።
- በጨረታው ለተሸነፈ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስለታል።
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን የጨረታ ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
- ያሸነፈበትን የጨረታ ገንዘብ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ ካላደረገ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ በድጋሚ ማስታወቂያ ወጥቶ ጨረታ ይካሔድበታል።
- ጨረታውን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የስም ዝውውር በፍ/ቤቱ ትእዛዝ ይፈጸምለታል።
- የጨረታው ሒደት የሚካሔደው 25/11/2018 ዓ/ም 4፡00-6፡00 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ከተማ መናኸሪያ ክ/ከተማ ሚሊኒየም ቀበሌ ውስጥ በአፈፃፀም ተከሳሽ አቶ ብርሃኑ ታደሰ ሻመሮ ስም ተመዝግቦ የሚታወቀው የመኖሪያ ቤት የሚገኝ ቅጥር ግቢ እንደሆነ አውቀው በተባለው ጊዜ እንድትገኙ ፍ/ቤቱ አዟል።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስር የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-01
- Publishing entity: Hawassa City High Court
- Bid bond: 25%
- Published: Jun 30, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.