የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትም/ቢሮ በተለያዩ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማሪያነት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ የላብራቶሪ ኬሚካሎች ጊዜያቸው ያለፈባቸውን በከተማችን ከሚገኙ ከተለያዩ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለማስወገድ የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መፈፀም ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 08/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትም/ቢሮ በተለያዩ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማሪያነት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ የላብራቶሪ ኬሚካሎች ጊዜያቸው ያለፈባቸውን በከተማችን ከሚገኙ ከተለያዩ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለማስወገድ የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መፈፀም ይፈልጋል።
ጨረታውን ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ የተጠቀሰውን ኬሚካሎችን ለማስወገድ በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣በጨረታ ለማሳተፍ የሚያበቃ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
2. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ በተመሰከረ /CPO/ 100,000.00 / አንድ መቶ ሺ ብር ለተጠቀሰው አገልግሎት ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከቢሮአችን ከመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 102 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት እና ሰነዱን በሶፍት ኮፒ ፣ በኢሜል ወይም በፍላሽ መውስድ ይችላሉ፣
4. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦርጂናልና ኮፒ ሰነድ ፖስታ በመለየት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር ከጧቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመንግስት ግዥ ዳይሬከቶሬት ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፣
5. ጨረታው በአየር ላይ ከዋለ በ11ኛው ቀን / በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው ቁጥር 101 ይከፈታል፤ ሆኖም ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፣
6. የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ከ7 ቀናት በኋላ ይመለሳል።
7. የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በፅሁፍ ከተገለፀ ከ7/ ሰባት/ ቀናት በኋላ እስከ 15 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ ወዲያውኑ ወደ ዳይሬክቶሬቱ መጥቶ ውል መፈረም አለበት ይህ ባይፈፅም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
8. አሸናፊው ድርጅት ውል ከፈፀመ በኋላ በውሉ መሰረት በሚሰጠው ትእዛዝ መሰረት አገልግሎት ለማቅረብ ዝግጁ መሆን አለበት።
9. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ
በስልክ ቁጥር 011 122 6456
አድራሻ 6 ኪሎ ወደ ጃንሜዳ መንገድ ኦሮሚያ ፍ/ቤት ፊት ለፊት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-07-13
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአየር ላይ ከዋለ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-07-13 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በአየር ላይ ከዋለ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa City Administration Education Bureau
- Buyer address: 6 ኪሎ ወደ ጃንሜዳ መንገድ
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Jul 01, 2026
- Posted at: 2026-07-01T07:45:05.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.