የሆሳዕና ማረሚያ ተቋም 44 እና ተሳፋሪዎችን የመጫን አቅም ያለው መካከለኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የመኪና አገልግሎት ትራንስፖርት ኪራይ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል
Description
ለመኪና ትራስፖርት አገልግሎት ኪራይ በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ሆማተ/2557/2018
የሆሣዕና ማረሚያ ተቋም የህግ ታራሚዎችን እና የፖሊስ ሰራዊቱንና ሠራተኞቹን ተቋሙ ባዘጋጀው የድርጊት መርሃ ግብር መሠረት በየቀኑ ከጠዋቱ 12፡30-11፡30 ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ድረስ የሚያመላልስ እንዲሁም ከመደበኛ ሰርቪስ ሥራዎች በተጨማሪ ቅዳሜ፣ እሁድና የበዓል ቀናት እንደአስፈላጊቱ ጥሪ ሲደረግ መጥቶ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን በመገንዘብ ፤ ከተማው ወደ ማረሚያ ተቋም ድረስ ከ07 ኪ/ር ደርሶ መልስ ሰርቪስ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል፤ ከዚህ በታች በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከተውን መካከለኛ የህዝብ ማመላለሻ የትራንስፖርት አገልግሎት ኪራይ መስፈርቱን ከሚያሟሉ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን /ግለሰቦችን/ ከሀምሌ 1/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 30/2019 ዓ/ም ድረስ ለስድስት ወራት በሚቆይ የማዕቀፍ ስምምነት፤ በውል ሰጪና በውል ተቀባይ መካከል በሚደረገው የውል ስምምነት መሠረት የሰርቪስ የአገልግሎት ጊዜውን እንደአስፈላጊነቱ ከ01 ወር እስከ 06 ወራት ተጨማሪ ጊዜ ለማራዘም እንደሚቻል ታሳቢ ባደረገ መልኩ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የመኪና አገልግሎት ትራንስፖርት ኪራይ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የአገልግሎቱ/አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
|
01 |
44 እና ተሳፋሪዎችን የመጫን አቅም ያለው መካከለኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ |
በቁጥር |
01 |
መመዘኛ መስፈርቶች፣
1. በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወቀረት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ የVAT 15% ምዝገባ ማስረጃ፤ የባለቤትነት ማረጋገጫ መታወቂያ (ሊብሬ)፤የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ፤ እንዲሁም የ3ኛ ወገን ኢንሹራንስ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ሰርተፍኬት ያለው/ላት፤ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈለ/ለች ፤
2. ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሆሣዕና ማረሚያ ተቋም ግዥና ፋይናንስ ንብ/አስ/የሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ለዚሁ ግዥ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በነፃ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ የጨረታ ማስከበሪያን በሚመለከት የብር 7,000/ሰባት ሺህ /ብቻ CPO ዋስትና ሰነድ በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
3. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አሥር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ተሞልቶ ከሙሉ ሰነዶች ጋር እንዲሁም ከላይ በተራ ቁጥር (01) ላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒዎች ጋር በታሸገ ኤንቬሎፕ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የንግድና ሌሎች ኮፒ ማስረጃዎች ላይ አጠራጣሪ ነገሮች ከታዬ ኦርጅናል ማስረጃዎችን አስቀርቦ የመጣራት እና የማረጋገጥ የተቋሙ ኃላፊነት ሆኖ ተጫራቾቹም ኦርጅናል ማስረጃዎችን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
5. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በማረሚያ ተቋሙ ግዥና ፋይናንስ/ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ወይም ተመሳሳይ አዳራሽ የሚከፈት መሆኑን ስንገልጽ፤ ዕለቱ የበዓላት /የዕረፍት/ ቀን ከሆነ በማግስቱ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
6. ተወዳደሪዎች በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፤
7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0926 200 823 ወይም 0912 052 832 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የሆሳዕና ማረሚያ ተቋም
Tender details
- Deadline: 2026-07-10
- Publishing entity: Hosaena Correctional Facility
- Bid bond: 7,000.00 ብር
- Published: Jul 01, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.