የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ዝናቤ ሲሳይ እና በፍ/ባለዕዳ እነ አቶ ነጋሽ ሄይ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.184668 በ03/10/2016ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.209946 በ30/7/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 9999/1/አዲስ/ በቁጥር YK117184459208272 የተመዘገበ ካርታ ያለው የይዞታ ስፋት 208 ካ/ሜ በልኬት የተገኘው የቦታ ስፋት 236 ካ/ሜ ሲሆን ይህን በልኬት የተገኘ ስፋት በስተምስራቅ በኩል በከፊል ከአጎራባች ጋር ያለው ድንበር በወሰናቸው መሰረት የታጠረ ባለመሆኑ በልኬት የተገኘው የቦታ ስፋት ሊቀነስ ወይም ሊጨመር የሚችል ሆኖ ከአጠቃላይ ይዞታ በካርታ ከተያዘው ላይ 6ኛ ዙር የመንገድ ጥናት 9.56 ካ/ሜ ይነካዋል በካርታ መሰረት በሐራጅ የሚሸጠው በብሎኬት የተሰራ 3 ክፍል ሰርቪስ ቤቶች ወይም የ6ኛ ተስማሚ የአቶ ተመስገን ፋንታሁን ሲሳይ ቤት የተባለውን ሳይጨምር የ6ኛ ተስማሚ አመቶ ተመስገን ፋንታሁን 3 ክፍል ብሎኬት የተሰራውን ቤት ሳይጨምር እና 3 ክፍል በብሎኬት የተሰራው የግል ቤት ስፋቱ 34.60ካ/ሜ ከቦታው ለቤቱ (3 ክፍል ብሎኬት ቤቱ) በንጽጽር የሚደርሰው የይዞታው ስፋት 25.97ካ/ሜ የሆነ የሐራጅ መነሻ 5,902,340 ( አምስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሁለት ሺህ ሶስት መቶ አርባ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትጵዮያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.P.O የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሽጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-04
- Bid closing time: 11:30
- Bid opening: 2026-08-04 11:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Jul 01, 2026
- Posted at: 2026-07-01T07:59:48.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.