ሪፍት ቫሊ ችልድረን ኤንድ ውመን ዲቨሎፕመንት ኦርጋናዜሽን የድርጅቱን በዋናው መ/ቤት ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ የመስክ መኪኖቹን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የመኪኖች የጨረታ ማስታወቂያ

ሪፍት ቫሊ ችልድረን ኤንድ ውመን ዲቨሎፕመንት ኦርጋናዜሽን የድርጅቱን በዋናው መ/ቤት ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ የመስክ መኪኖቹን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም፡-

ተጫራቾች

1. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መኪኖቹ በሚገኙበት አድራሻ ጉርድ ሾላ ቴን ሲሰተር ህንፃ ግቢ ውስጥ መመልከት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የሚገዙትን መኪና ወይም ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አስርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል።

3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል።

4. ተጫራቾች የመኪናውን ዝርዝር የያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ /column/ስር የሚገዙበትን ዋጋ በአኀዝና በፊደል ያለ ሰርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ አዲስ አበባ ከተማ ጉርድ ሾላ ኤኤች ኤፍ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 304 በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት አስተዳደርና ፋይናንስ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ ወይም በተወካዩ መፈረም አለበት።

5.ተጫራቾች ጨረታው በተለያዩ የማስታወቂያ ሰሌዳዎችና በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 07(ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ መውሰድ አለባቸው።

6. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ03 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በ5ቀናት ውስጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።

7. ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ለአንድ መኪና የማይመለስ 500 ብር (አምስት መቶ ብር) እየከፈሉ ባሉት 07 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እስከ ሰባተኛው ቀን 6፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ። ለተጨማሪ መኪና መጫረት ከፈለጉ ተጨማሪ ሰነድ መግዛት አለባቸው።

8. የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ወይም በተለያዩ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 07 (ሰባት) የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በሰባተኛው ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 10፡00 ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፊት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

9. ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነድ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ።

10. ድርጅቱ ላሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-647 8382/09 20 52 37 34 ወይም በአካል በመምጣት መጠየቅ ይቻላል። ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ጉርድ ሾላ ኬ.ኤች.ኤፍ ሕንፃ ቢሮ ቁጥር 304

ሪፍት ቫሊ ችልድረን ኢንድ ውመን ዲቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-07-08
  • Bid closing time: 15:30
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ወይም በተለያዩ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰባተኛው ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-08 16:00
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ወይም በተለያዩ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰባተኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Rift Valley Children and Women Development Organization (RCWDO)
  • Bid bond: 20%
  • Bid document price: 500.00 ብር ለአንድ መኪና
  • Published: Jul 01, 2026
  • Posted at: 2026-07-01T08:08:52.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders