ገዳ ባንክ አ.ማ. የቦታ ስፋት በካ.ሜ 109.14 የሆነ የመኖሪያ ቤት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ማስታወቂያ

ቁጥር፡- 003/3/2018

ገዳ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/1992 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን ከታች በሰንጠረዡ የተገለጸውን ቤት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የተበዳሪው ስም

የንብረት አስያዥ ስም

ጨረታ የቀረበ ንብረት ዓይነት

አበዳሪው ቅርንጫፍ

 

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት

የጨረታ መነሻ ዋጋ

የጨረታ ቀንና ሰዓት

ጨረታው የወጣው

ከተማ

ቀበሌ/ ወረዳ

የባለቤትነት ማረጋገጫ ቁጥር

የቦታ ስፋት  በካ.ሜ

ቀን

ሰዓት

ሪኖ ዋን ትሬዲንግ /የተ/የግ/

ናሆም ዳዊት ሀሰን

 

የመኖሪያ ቤት

ዶሎ

ቢሾፍቱ ከተማ ድባዩ /ከተማ

ደካ ቦራ

 

OR003074513013

 

109.14

 

12,094,783.00

 

25/11/2018

 

3:0-4:00

 

ለሁለተኛ ጊዜ

  1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ/ሲ.ፒ.ኦ አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል። በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል።
  2. ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ ጎተራ ወንጌላዊት ህንፃ አከባቢ በሚገኝ ገዳ ባንክ ህንፃ 7ኛ ፎቅ ላይ ይካሄዳል። በዕለቱ ባለ ዕዳዎች እና ታዛቢዎች ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል።
  3. ድርጅቶች ጨረታው ላይ ለመሳተፍ ተረጋግጦ የተመዘገበ የመመስረቻ ፅሁፍ እና እንደአስፈላጊነቱ መተዳደሪያ ደንብ እና ቃለ-ጉባኤዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝጊያ በፊት ይጠናቀቃል። የጨረታ መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች ካልተለየ አስኪለይ ድረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል።
  5. በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከባንኩ የህግ አገልግሎት መምሪያ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል።
  6. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል። በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚፈጠረው ልዩነት ይጠየቃል።
  7. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
  8. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር፣ የሊዝ ክፍያ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የስም ማዛወሪያ እና ማናቸዉም ከጨረታው ጋር በተገናኘ መንግስት የሚጠይቀውን ክፍያ ይከፍላል።
  9. የጨረታው አሸናፊ በንብረቱ ላይ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ የሚከፈለውን ክፍያ ለመክፈል ንብረቱ በሚገኝበት ወረዳ ወይም ከተማ አስተዳደር በመቅረብ የሊዝ ውል መዋዋል አለበት።
  10. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዘው ለመጎብኘት ይችላሉ።
  11. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 20 88 57 34 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
  12. ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Tender details

  • Deadline: 2026-08-01
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-01 10:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Gadaa Bank S.C.
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jul 01, 2026
  • Posted at: 2026-07-01T08:46:17.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders