ስፋቱ 250 ካ.ሜ የሆነ መኖሪያ ቤት ሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአፈ/ከሳሽ ወ/ሮ የሽወርቅ ጌጡ እና በተከሳሽ አቶ ዩሐንስ ጌትነት መካከል ባለው የባልና ሚስት የአፈጻጸም ክስ ክርከር ጉዳይ የአፈ/ተከሳሽ አቶ ዮሐንስ ጌትነት በስማቸው በዳግማዊ ሚኒልክ ክፍለ ከተማ ፍኖተ ቀበሌ ተመዝግቦ የሚገኘው በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ዮሴፍ የቆየ፣ በሰሜን ኢለኒ ደረጀ እንዲሁም ምትኩ ከበደ መካከል የሚገኝ 250 ካ.ሜ የመኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ 4,663,549.78 (አራት ሚሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ ሶስት ሺህ አምስት መቶ አርባ ዘጠኝ ብር ከሰባ ስምንት ሳንቲም) በጨረታ ይሸጣል።

ስለሆነም መጫረት የምትፈልጉ ሁሉ የጨረታ መነሻ ዋጋውን በመያዝ ከጨረታው ቦታ በመገኘት መጫረት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው ከሰኔ 29/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም ለ30 ቀናት የሚቆይ ሆኖ ሀምሌ 30/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡00 እስከ 7፡00 ከላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ንብረቱ ካለበት ቦታ ፍኖተ ቀበሌ ድረስ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል።

ማሳሰቢያ፡- የጨረታው አሸናፊው ¼ ኛውን በእለቱ የሚያስይዝ ቀሪውን ገንዘብ በቀጠሮ ቀን ይዞ የሚቀርብ መሆን አለበት

የባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-06
  • Publishing entity: Bahir Dar City Woreda Court
  • Published: Jun 29, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders