የቦታ ስፋት 57.77 ካ.ሜ ባለ አንድ መኝታ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ ባለመብት ሰይፉ ቶላ እና የፍ ባለዕዳ አቶ ሀይሌ ትዕዛዙ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/331583 በ10/02/2018 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ እና በኮ/መ/ቁ/05248 በ23/4/2018ዓ/ም እና በቀን በ24/6/2018 ዓ.ም በኮ/መ/ቁ/19056 በ14/7/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ህንጻ ቁጥር 23 የወለል ቁጥር 8ኛ የቤት ቁጥር BBL1-B23/HN/803 የይዞታ መለያ ቁጥር AA000061207402230803 የቦታ ስፋት 57.77 ካ.ሜ ባለ አንድ መኝታ ቤት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 2,273,943 (ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰባ ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ሶስት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-05
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-08-05 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Jul 02, 2026
- Posted at: 2026-07-02T07:22:50.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.