የአርባ ምንጭ ከተማ ፋይናንስ እና ፕላን ልማት መምሪያ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት አርባ ምንጭ ሪጂዮ ፖሊሲ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መምሪያ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ግዥ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የዕቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የአርባ ምንጭ ከተማ ፋይናንስ እና ፕላን ልማት መምሪያ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት አርባ ምንጭ ሪጂዮ ፖሊሲ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መምሪያ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ግዥ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል።

1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው የግብር ከፋይ ቁጥር (TIN No) ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ

2. አቅራቢነት ማስረጃ ኦን ላይን ማቅረብ የሚችል፣

3. ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ለአንድ ጨረታ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ እና ከጨረታው ማስከበሪያ የምፈቅደውን ማስያዝ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።

4. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአ/ም/ከ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ ብር 3000.00 /ሦስት ሺህ ብር / በመክፈል የጨረታ ሰነድ እንድትገዙ እንገልፃለን።

5. ዋጋቸውን በማያሻማ መልኩ እንድታቀርቡ እናሳውቃለን።

6. ጨረታው በጨረታ ሣጥን የሚገባው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን የሚከፈተው በእለቱ 4፡30 በከተማው በፋ/ፕ/ል/መምሪያ ይሆናል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዕረፍት ከሆነ በቀጣይ ቀን ይሆናል።

7. ተጫራቾቹ ጨረታ ዶክመንት ቴክኒካል 1 ኦርጂናል 1 ኮፒ እና ኮፒ 2 ፋይናንሻል ኦርጂናል እና ኮፒ 1 እና ኮፒ 2 በእናት ፖስታ ታሽጎ እንዲቀርብ

8. ውል ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችል፣

9. አሸናፊው ዕቃውን የሚያስረከብበት ቦታ በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ግቢ ውስጥ ሲሆን ማስጫኛና ማውረጃ የትራንስፖርት ወጪዎች በአሸናፊው ይሸፈናል።

10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፏቸውን ዕቃዎች ናሙና የማቅረብና የማስያዝ ግዴታ አለበት።

11. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

12. የዕቃው መጠን በሰነዱ ላይ በተገለፀው መሠረት በ20% ሊጨምርም ሆነ ሊቀንስ ይችላል።

13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።

14. አሸናፊ ድርጅት ቴክኖሎጂዎችን ሙሉ እቃዎችን አቅርቦ ገጥመው መስራቱን አረጋግጦ መስጠት ይኖርበታል። ለሁለት ዓመት ዋስትና ማስያዝ ወይም በፍትህ መምሪያ ቀሪበው የውል ሰነድ መፈረም የሚችል መሆን አለበት።

15. የፋይናንሻል ውጤት በተመለከተ የአጠቃላይ ዕቃዎች ድምር ይሆናል።

የአርባ ምንጭ ከተማ ፋይናንስ እና ፕላን ልማት መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-17
  • Publishing entity: የአርባ ምንጭ ከተማ ፋይናንስ እና ፕላን ልማት መምሪያ
  • Bid bond: 500,000.00 ብር ለአንድ ጨረታ
  • Bid document price: 3,000.00 ብር
  • Published: Jul 02, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders