Property and building foreclosure

የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የአንደኛ ደረጃ የሐራጅ ማስታወቂያ

በአፈ/ከሳሽ አቶ አራጋው ዘዋለ እና በአፈ ተከሳሽ አቶ ላቄ ስጦታው መካከል የአፈጻፀም ክርክር ክስ ጉዳይ ከፍ/ፍ/ቤት የሰኔ 15 ቀን 2018 ዓም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ መሰረት የአፈ ተከሳሽ በፍርድ የተወሰነውን ብር 2,404000 (ሁለት ሚሊየን አራት መቶ አራት ሺ ብር) መክፈል ባለመቻላቸው ምክንያት በሻሁራ ከተማ አስተዳያር የሚገኝ የቦታ ስፋት 400 ካሬ ሜትር የሆነ በአዋሳኝ ፤ በምስራቅ የሻንበል አክሊሉ እና አዲስ ገጽ፣ በሰሜን ፈቃዴ መለሰ፣ በምእራብ መንገድ፣ በደቡብ መንገድ የሚያዋስነው ቤትና ቦታ በመነሻ ዋጋ 1,409,576.94 / አንድ ሚሊየን አራት መቶ ዘጠኝ ሺ አምስት መቶ ሰባ ስድስት ብር ከዘጠና አራት ሳንቲም /በሆነ መነሻ ዋጋ በግልጽ ጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ ወስኗል በመሆኑም ከላይ በአዋሳኝ የተጠቀሰውን ቤት እና ቦታ መጫረት (መግዛት) የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ሁሉ ሀምሌ 24 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡3ዐ እስከ ቀኑ 6፡30 ሰዓት ድረስ ቤቱ ከሚገኝበት ቦታ ድረስ በመቅረብ ቤትና ቦታውን አይቶ መጫረት እና መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች እንድታሟሉ እንገልጻለን።

  1. ተወዳዳሪዎች ከጠዋቱ 3፡30 ሠዓት እስከ ቀኑ 6፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ቤቱን እና ቦታን አይቶ መቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

2. ገዥ ሲያሸንፍ አንድ አራተኛውን ወዲያውኑ ያስይዛል።

3. ገዥ ሲያሸንፍ በ15 ቀን ውስጥ አጠቃሎ ከከፈለ ስመ-ንብረቱ ወዲያውኑ እንዲዛወርለት ይደረጋል።

4. የጨረታ ተወዳዳሪዎች በጨረታ ወቅት መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. በጨረታ የሚወዳደሩ ራሳቸው ወይም ህጋዊ ወኪላቸው ይሆናል።

6. በጨረታ ወቅት ሁከት የሚፈጥር በህግ ይጠየቃል።

7. ስመ ንብረት ማዛወሪያ በጨረታ አሸናፊው የሚሸፈን ይሆናል።

8. ጨረታው በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐራጅ ባይ የሚመራ ይሆናል።

ከዚህ በላይ በዝርዝር የቀረበውን አሟልታችሁ ለመወዳደር የምትፈልጉ ሁሉ ቤቱ ከሚገኝበት ሸሁራ ከተማ ቤቱንና ቦታውን በአካል ቀርበው በማየት በጨረታው ቀን እና ሰዓት በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን የማእ/ጎን/ዞን ከፍ/ፍ/ቤት አዟል።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-31
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid opening: 2026-07-31 09:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: የማእከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
  • Published on: Addis Zemen (Jul 03, 2026)
  • Posted at: 2026-07-03T07:31:03.000Z
← Back to all tenders