የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ካምፓስ ባዘጋጃቸው የካፌና ሬስቶራንት የአገልግሎት መስጫ ህንጻ 843 ለተማሪዎች አገልግሎት እንዲሰጡ በኪራይ ህንጻ ለማከራየት በካፌና ሬስቶራንት ዘርፍ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን በማወዳደር ለሶስት አመት ማከራየት ይፈልጋል

Description

ድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ብግጨ 04/2018

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ካምፓስ ባዘጋጃቸው የካፌና ሬስቶራንት የአገልግሎት መስጫ ህንጻ 843 ለተማሪዎች አገልግሎት እንዲሰጡ በኪራይ ህንጻ ለማከራየት በካፌና ሬስቶራንት ዘርፍ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን በማወዳደር ለሶስት አመት ማከራየት ይፈልጋል።

በመሆኑም በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣እና የቲን ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማቅረብ የሚችሉ፣

1. ለስራ የሚያስፈልጉ የሰው ሀይል እና መሳሪያ ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ በራሱ ማቅረብ የሚችል፣

2. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00/አንድ መቶ ሽህ/ ብር ወይም በጥቃቅን የተደራጁ ከአደራጃቸው የመንግስት መ/ቤት የዋስትና ደብዳቤ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም በማሠራት ማቅረብ የሚችሉ፣

3. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀለት ከ7/ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ወይም የዋስትና ደብዳቤ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ8 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ የሚችል መሆን አለበት፣

4. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቴዎድሮስ በካፋ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 012 እና አዲስ አበባ አራት ኪሎ ከቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ ሮሚና ካፌ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በመቅረብ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደ/ማ/ዩ 1000017980517 በማስገባት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፣፣

5. ተወዳዳሪ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሸግ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡59 ድረስ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቴዎድሮስ በካፋ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 012 ድረስ በመቅረብ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣

6. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቴዎድሮስ በካፋ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 012 ድረስ በግዥ ቡድን ቢሮ ይከፈታል።

7. የጨረታውን ፋይናንሽያል ኦርጅናል የጨረታ ማስከበሪያና ኮፒ ዶከመንቶችና ለየብቻ አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ በማድረግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተም በማድረግ በተጠቃለለ አንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸው።

8. ዩኒቨርሲቲው ውስጥ በተለያዩ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ በስማቸው በጨረታው መሳተፍ አይችሉም።

9. ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሣሰቢያ፡- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀናት ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-13
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
  • Bid opening: 2026-07-13 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Debre Markos University
  • Buyer address: Debremarkos University
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jul 03, 2026
  • Posted at: 2026-07-03T07:34:29.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders