በሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት የበንሳ ዳዬ ማረሚያ ተቋም ለሕግ ታራሚዎች የምግብ አገልግሎት የሚውል ጥሬ እህል ለ2019 በጀት ዓመት ከሐምሌ 2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 2019 ዓ/ም/ ድረስ ለሕግ ታራሚዎች ቀለብ የሚውል ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት የበንሳ ዳዬ ማረሚያ ተቋም ለሕግ ታራሚዎች የምግብ አገልግሎት የሚውል ጥሬ እህል ለ2019 በጀት ዓመት ከሐምሌ 2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 2019 ዓ/ም/ ድረስ ለሕግ ታራሚዎች ቀለብ የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘረውን የምግብ ጥሬ እህሎች ለመግዛት ይፈልጋል፡-
- ነጭ ጤፍ አንደኛ ደረጃ በፍሬ በኩንታል
- 1ኛ ደረጃ በቆሎ በነቀዝ ያልተበላ በፍሬ በኩንታል
- 1ኛ ደረጃ ባቄላ በነቀዝ ያልተበላ በፍሬ በኩንታል
- 1ኛ ደረጃ ፍኖ ፉርኖ/ ዱቄት በኩንታል
- ዛላ በርበሬ 1ኛ ደረጃ
- ቀይ ሽንኩርት ጥራቱን የጠበቀ
- ነጭ ሽንኩርት
- ካሜራ ትልቁ ባለ500 ግራም
- ካሜራ ትንሹ ባለ 19 ግራም
- ሻይ ቅጠል ባለ 40 ግራም
- ሻይ ቅጠል ባለ 80 ግራም
- አዮዲን ጨው
- ጎመን ዘር ያልተፈጨ ( በፍሬ)
- አክንባሎ
- የአፈር ምጣድ
- ምስር
- ሰፌድ
- የማገዶ እንጨት
- በሚወዳደሩበት መስክ የ2018 ዓ/ም የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት ማስረጃ ያላቸው፤ የ2018 ግብር አጠናቀው የከፈሉና ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ፤ ከመንግስት ዕዳ ነፃ ስለመሆናቸውና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ
2 .በጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን እህሎች ለ6 ወራት የሚፈለገውን መጠን ጥራትና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በየወሩ እስከተቋሙ ቅጥር ግቢ ድረስ አምጥተው ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
3.ማንኛውም ተጫራች በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠየቀውን ሕጋዊ ማስረጃዎች ለጨረታ ከሚያቀርበው ዋጋ ጋር ዋናውንና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ የያዘ ሲፒኦ /CPO/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ እንዲሁም ጥሬ ገንዘብ በማያያዝ ከዋናው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ከሞሉ በኃላ የጨረታውን ሠነድ አንድ ኦርጂናል እና አንድ ፎቶ ኮፒ ሰነድ በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው እንደገና በአንድ ትልቅ ኤንቬሎፕ ውስጥ አስገብተው በኤንቬሎፑ ላይ የተጫራቾች ድርጅት ማህተም አርፎበት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ አስራ አንደኛው ቀን 8.00 ሰዓት ድረስ ኤንቨሎፑን ወደ ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. በዚሁ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8.30 ሰዓት የጨረታ ሣጥኑ ከታሽገ በኋላ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት በበንሳ ዳዬ ማረሚያ ተቋም ግዥና ንብረት አስ/ር ስራ ሂደት ይከፈታል። እንደ አጋጣሚ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
7. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከመከፈቱ አንድ ቀን ሲቀረው የእህል ናሙናውን ለጨረታ ኮሚቴው መስጠት አለበት።
8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 / ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከግዥና ንብረት አስ/ር ስራ ሂደት መግዛት ይችላሉ።
9. የሚቀርበው የዕቃ ብዛት በጨረታ ሠነዱ ላይ የተመለከተ ስለሆነ ተወዳዳሪዎች ዝርዝር የጨረታ መመሪያውን በሚገባ በማንበብ መወዳደር ይኖርባቸዋል።
10. የጨረታው አሸናፊ ከአሸነፈበት ጊዜ ጀምሮ ውሉን የማይፈጽም ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ አይመለስም። ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 13 56 48 59 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የበንሳ ዳዬ ማረሚያ ተቋም ዳዬ
Tender details
- Deadline: 2026-07-14
- Publishing entity: Bensa Daye Correctional Facility
- Bid bond: 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jul 04, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.