አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. መኖሪያ ቤት ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ድሬዳዋ ዲስትሪክት ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን ከታች በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ንብረቱን ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
  • ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀን እና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
  • ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
  • በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
  • የጨረታ ቦታ ሶማሌ ክልል፣ ጅጅጋ ከተማ፣ ቀበሌ 13 ውስጥ በሚገኘው አቢሲንያ ባንክ ጅጅጋ ቅርንጫፍ ውስጥ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 254 11 07 75 ድሬደዋ እና +2519 15 33 70 71 ጅጅጋ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
  • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

.

የተበዳሪው ስም

የመያዣ ሰጪው ስም

የንብረቱ አይነት እና አገልግሎት

የቦታው ስፋት በካ.

የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር

ጨረታው የሚካሄድበት ቀን

የምዝገባ ሰዓት ጠዋት ..

የጨረታ ሰዓት ጠዋት ..

የወጣበት ጊዜ

1.

/ ኢስመሃን ኡመር አሊ

/ ኢስመሃን ኡመር አሊ

ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል የመኖሪያ ቤት

400

K/38434/2016

ሶማሌ ክልል፣ጅጅጋ ከተማ፣ ቀበሌ 13

 

5,188,075.58

ነሀሴ 01 ቀን 2018 .

3:30-4:30

4:30-5:30

ለመጀመሪያ ጊዜ

 


Tender details

  • Deadline: 2026-08-07
  • Bid closing time: 11:30
  • Bid opening: 2026-08-07 11:30
  • Region: Somali
  • Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
  • Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jul 05, 2026
  • Posted at: 2026-07-06T08:39:58.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders