ኬኬ ኃላ/የተ/የግ ኩባኒያ የሕንፃ ኪራይ ማከራየት ይፈልጋል
Description
የሕንፃ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
ኬኬ ኃላ/የተ/የግ ኩባኒያ ካስገነባቸው ዘመናዊ ሕንፃዎች መካከል የአፍሪካ ገበያ ማዕከል በሆነው ከመርካቶ በቅርብ ርቀት በሚገኘው በተለምዶ ጨው በረንዳ ተብሎ በሚጠራው እና በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ውስጥ ባለ 5 ወለል ዘመናዊ ህንፃ አጠናቆ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ሙሉ ሕንፃውን ለአንድ ተጫራች ማከራየት ይፈልጋል።
ሕንፃው የውሃ፣ የኤሌክትሪክ፣ የኢንተርኔት ዝርጋታ የተሟላለት ከመሆኑም በላይ ለአካል ጉዳተኞች እና ለአቅመ ደካሞች ዘመናዊ ሊፍት የተገጠመለት ሲሆን የመኪና ማቆሚያ አያሳስቦት፣ ከ50 በላይ መኪኖችን ማስተናገድ የሚችል የመኪና ፓርኪግን ያካተተ ነው፡፡
ለሚከራዩት ሕንፃ ከስርቆት ስጋት ነፃ እንዲሆኑ ኬኬ በራሱ ወጪ አስተማማኝ የ24 ሰዓት ጥበቃ እና ዘመናዊ ካሜራ አስገጥሟል።
እናስ ምን ይጠብቃሉ? ይፍጠኑ ይህን እንከን የለሽ ዘመናዊ ሕንፃ ሳያመነቱ ይከራዩ። ሕንፃው ለባንክ አገልግሎት፣ ለኢንሹራንስ፣ ለገንዘብና ብድር ተቋማት እንዲሁምለትምህርትና ጤና አገልግሎት፣ ለሱፐርማርኬት ምቹ በመሆኑ ፍላጎት ያላችሁ በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛቹኋል።
የጨረታ ሰነዱን ለማግኘት ሕንፃው በተገነባበት በጨው በረንዳ ቢሮአችን በመምጣት፤ ለጨረታ ሰነዱ መግዣ የማይመለስ አንድ ሺ ብር (1,000) በመክፈል ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ።
ጨረታው ይሕ ማስታወቂያ ከወጣበት ወይም ከተነገረበት ከ ሰኔ 26/2018 ዓ.ም. ቀን አንስቶ ለአሰር ተከታታይ የስራ ቀናቶች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ ጨረታው ሐምሌ 9/2018 ዓ.ም ምሽት 11 ሰዓት ተዘግቶ በበነጋታው ሐምሌ 10/2018 ዓ.ም. ተጫራጮች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፋታል።
ኬኬ ኩባኒያ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኛሉ።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0939-422324 / 0911- 248333 በስራ ሰዓት ብቻ ይደውሉ።
ኬኬ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ
Tender details
- Deadline: 2026-07-16
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-07-17 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: KK Private Limited Company
- Buyer address: ብሔራዊ አካባቢ ከቀድሞ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና፣ በወርቃማው ብሔራዊ ባንክ መሃከል ወደ ብሔራዊ ቤተ መዛግብት በሚወስደው መንገድ
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
- Published: Jul 04, 2026
- Posted at: 2026-07-06T08:51:59.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.