የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ንብረቶችን ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

1. በድጋሚና አዲስ የወጣ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች ጨረታ ቁጥር 01/2026/27

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ንብረቶችን ማለትም የቶዮታ ተሽከርካሪ የኤሌክትሪካል መለዋወጫዎች፣ የቶዮታ ተሽከርካሪ የመካኒካል መለዋወጫዎች፣ የሞተር ሳይክል መለዋወጫዎች፣የሞተር ሳይክል ከመነዳሪዎች፣ የተለያዩ ያገለገሉ ፈርኒቸር ንብረቶች፣ የተለያዩ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የተቃጠለ የሞተር ዘይት ከነበርሜሉ ባሉበት ሁኔታ በድጋሚና አዲስ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

1. ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን ሰነድ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 211 የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።

2. ተጫራች ያገለገሉ ንብረቶችን ከሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ያገለገሉ ንብረቶችን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ትይዩ ባለው አስፓልት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው የቀድሞ ብራሌ ጥጥ መዳመጫ ግቢ ውስጥ እና የተሽከርካሪ፣ የሞተር ሳይክል መለዋወጫ እና የተቃጠለ የሞተር ዘይት  የሚገኘው ቃሊቲ ከመንገድ ትራንስፖርት የማሽከርከር ብቃት ማረጋገጫ እና ማሰልጠኛ ተቋም አጠገብ በሚገኘው የባንኩ ተሽከርካሪዎች ጥገና ጋራዥ /የቀድሞው አማልጋ ሜትድ/ ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ ከ2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በመገኘት ማየት ይችላል።

3. የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ታዛቢዎች በተገኙበት ይታሸጋል።

4. ተጫራች ለንብረቱ የሚሰጠውን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ክፍት ቦታ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎችም አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ያስገባል።

5. የተለያዩ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የተቃጠለ የሞተር ዘይት ምድቦች ላይ የሚሳተፍ ተጫራች በጨረታ ለመሳተፍ ከኢፌድሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የተቃጠለ የሞተር ዘይት የማስወገድ ወይም መልሶ የመጠቀም ፈቃድ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል ብቻ መሆን አለበት።

6. ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2ኛ በግልጽ ይከፈታል።

7. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ሲፒኦ አሸናፊ ለሚሆነው በሚገዛው ንብረት ክፍያ ላይ የሚታሰብ ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

2. በድጋሚ የወጣ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ጨረታ ቁጥር 02/2026/27

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብዛታቸው 18 የሆኑ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በድጋሚ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

8. ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን ሰነድ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 211 የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።

9. ተጫራች ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ከሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ቃሊቲ ከመንገድ ትራንስፖርት የማሽከርከር ብቃት ማረጋገጫ እና ማሰልጠኛ ተቋም አለፍ ብሎ በሚገኘው በባንኩ የተሽከርካሪ ጋራዥ /የቀድሞ አማልጋ ሜትድ/ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ ከ2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በመገኘት ማየት ይችላሉ።

10. የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ታዛቢዎች በተገኙበት ይታሸጋል።

11. ተጫራቾች ለተሽከርካሪው የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ክፍት ቦታ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በማያያዝና በፖስታ በማሸግ ልደታ አካባቢ በሚገነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛግዌ ሕንፃ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ሃምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 5፡00 ሰዓት ብቻ ያስገባሉ።

12.  ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው ልደታ አካባቢ በሚገነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛግዌ ሕንፃ መሰብሰቢያ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል።

13.የተሽከርካሪዎቹ ዓይነትና የታርጋቸው ቁጥራቸውን የሚያሳይ ዝርዝር

S.No.

Types of Vehicles

Vehicles Plate Number

1

Nissan Sunny Automobile

ET-3-35096

2

Mitsubishi Lancer Automobile

ET-3-44053

3

Mitsubishi Lancer Automobile

ET-3-44074

4

Mitsubishi Lancer Automobile

ET-3-44075

5

Mitsubishi Lancer Automobile

ET-3-45061

6

Nissan Patrol

ET-3-40059

7

Nissan Patrol

ET-3-40066

8

Nissan Patrol

ET-3-40071

9

Nissan Patrol

ET-3-40072

10

Nissan Patrol

ET-3-40077

11

Nissan Patrol

ET-3-40079

12

Nissan Patrol

ET-3-40085

13

Nissan Patrol

ET-3-40087

14

Mercedes Van

ET-3-38913

15

Mercedes Van

ET-3-38914

16

Yamaha Motor Cycle

ET-4-0677

17

Bishoftu double pickup

ET-3-98853

18

Bishoftu double pickup

ET-3-98890

7.  ተጫራች ለሚጫረትበት የንብረት ዓይነቶች የጨረታ የመነሻ ዋጋውን 25% (ሃያ አምስት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለያገለገሉ ንብረቶች አስወጋጅ (Commercial Bank of Ethiopia Disposal) በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ሲፒኦ አሸናፊ ለሚሆነው በሚገዛው ንብረት ክፍያ ላይ የሚታሰብ ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


Tender details

  • Deadline: 2026-07-30
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-07-30 11:15
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Commercial Bank of Ethiopia
  • Bid bond: 25%
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published: Jul 05, 2026
  • Posted at: 2026-07-06T09:13:45.000Z
  • Buyer website: https://www.combanketh.com

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders