445 ካ.ሜ ቤትና ቦታ የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

Description

የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአፈ /ከሳሽ አስካል ሽመልስ ወኪል አዝራ ሽመልስ ጠበቃ ግዛው ከበደ እና በአፈ ተከሳሽ 1ኛ አሸነፍ ቢያበይን 2ኛ የተመኝ መለሰ መካከል ስላለው የገንዘብ አፈጻጸም ከስ ከርክር ጉዳይ በወልዲያ ከተማ 09 ቀበሌ ባዋሳኝ በምስራቅ ሞላ አድማሴ፣ በምዕራብ ያረጋል ቢያበይን 50 ሜትር መንገድ /ሸሽግ ቢያበይን፣ በሰሜን/ሽሽግ ቢያበይን፣ በደቡብ ቸኮለ መኮነን 445 ካ.ሜ ቦታ በ1ኛ አፈ/ተከሳሽ ከም ተመዝግቦ የሚገኘው ቤትና ቦታ ከዕዳና ዕገዳ ነፃ መሆኑ ታውቆ በጨረታ መነሻ ዋጋ 924,328.6 (ዘጠኝ መቶ ሃያ አራት ሺህ ሶስት መቶ ሀያ ስምንት ብር ከ60/00 ሳንቲም) በሀራጅ ጨረታ እንዲሸጥ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ስለዚህ የጨረታው ማስታወቂያ ከሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሀምሌ 28 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ 30 ቀን አየር ላይ ቆይቶ ጨረታው ሀምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ መግዛት የሚፈልግ በወልዲያ ከተማ 09 ቀበሌ ለጨረታ በወጣው ቤት ግቢ ውስጥ በመገኘት መግዛት መጫረት⁄ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታው አሸናፊ የጨረታ አሸናፊነቱን እንዳወቀ ወዲያውኑ ሃያ አምስት በመቶውን በሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስም በተከፈተው የአደራ ገንዘብ ማስቀመጫ አማራ ባንክ ወልዲያ ሂሳብ ቁጥር 9900005450938 በሆነ እንድታስይዙ ደረሰኙን ለሀራጅ ባይ ወዲያውኑ እንዲሰጡ እና ቀሪ ብሩን በአስራ አምስት ቀን ውስጥ ከፍሎ ማጠናቀቅ ያለበት መሆኑን እናሳውቃለን።

የሰሜን ወሎ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት

 

 


Tender details

  • Deadline: 2026-08-05
  • Publishing entity: North Wollo Zone High Court
  • Published: Jul 05, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders