በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት የአንደኛ ዙር ለቢሮ፣ አገልግሎት የሚውሉ ጥቅል ደረጃቸውን የጠበቁ እቃዎች እና አገልግሎቶች ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 005/002/2019

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት የአንደኛ ዙር ለቢሮ፣ አገልግሎት የሚውሉ ጥቅል ደረጃቸውን የጠበቁ

  • የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች፣
  • የጽዳት እቃዎች፣ 
  • የደንብ ልብሶች፣
  • ዶሮ የዶሮ ኬጂ የህንጻ መሳሪያ የጉልበት ስራ፣
  • የትራንስፖርት አገልግሎት የመኪና አላቂ ዕቃ
  • (የጽዳት ዕቃ)
  • ለአንድ አመት ኮንትራት የሚቆይ የተለያዩ የጥገና አገልግሎት፣
  • ህትመቶች
  • የመስተንግዶ 

አገልግሎቶች ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ በገ/ኢ/ሚኒስቴር ወይም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር ( supplier List ) ውስጥ የተመዘገቡበትን ምስክር ወረቀትና ማንኛውም ተወዳዳሪ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸው መረጃ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል ።
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አድርጎ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል ። በጨረታ መዝጊያ ሰዓት የሚመጡ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ማስታወቂያ ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃ ዓይነቶች በሙሉም ሆነ በከፊል መጫረት ይችላሉ ።
  5. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ ሊሆን ይገባል ።
  6. ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን ፣ አድራሻቸውን እንዲሁም ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ በመፈረም በማህተም ማረጋገጥ ይኖርባታል።
  7. ተጫራቾች በጨረታ የሚወዳደሩትን የዕቃ ዓይነቶች ለይተው መፃፍ አለባቸው።
  8. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠ ድርጅት ዕቃዎችን ከወረዳው አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ጋር ውል በገባ 10 ቀናት ውስጥ ዕቃ ግምጃቤት ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት አገልግሎት ወይም ወጪ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት ።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. የተጫረቱትን ዕቃ ዋጋ ጠቅላላ ድምር በሎት 2 % በካሽ ማሳያ ማዘዣ እና ኮፒ በተደረገበት የጨረታ ሰነድ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ።
  10.  በጨረታው ያሸነፈው አካል ማሸነፉን እንደተገለጸለት ከመ/ቤቱ ጋር በ10 (አስር) ቀን ቀርቦ ውል መፈጸም አለበት ።
  11. በጨረታው ያሸነፈ አቅራቢ ውል ከጽ/ቤቱ ጋር ውል ካልፈጸመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ. ተመላሽ አይሆንም ።
  12.  በጨረታው ያሸነፈ አቅራቢ ውል ቢፈጽም የግዢውን አጠቃላይ ዋጋ 2% ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል ።
  13. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ።
  14. የጨረታ ሳጥን በ 10ኛው ቀን ከቀኑ 10፡30 ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 ይከፈታል፤ 11ኛው ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
  15. በጨረታው ላይ የቀረበው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ባለው ተከታታይ ለ60 (ስልሳ ) ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል ።
  16.  መስሪያ ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0967670005/0911460014/0913147951

በመደወል ከድሪም ላይነር ሆቴል ወረድ ብሎ ወይም ከናዝራ ሆቴል ፊት ለፊት የድሮ 35 ቀበሌ ሦስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል።

የቂርቆስ ክ/ከተማ የወረዳ 02 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-16
  • Bid closing time: 16:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 10፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-17 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kirks Sub City Woreda 02 Administration Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: በሎት 2%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jul 05, 2026
  • Posted at: 2026-07-06T09:56:29.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders