ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር ተርማል ፔፐር (Thermal paper) ከአምራች ድርጅቶች ብቻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የተርማል ፔፐር (Thermal paper)ግዥ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር LT/HT/HO/08/2026
ሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ.
1. ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር ተርማል ፔፐር (Thermal paper ) ከአምራች ድርጅቶች ብቻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30-6፡00 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡ 30 -10፡00 ድረስ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30-6፡00 ድረስ ሕዳሴ ቴሌኮም አማ ጠመንጃ ያዥ ንግድ ባንክ አጠገብ ቴሌ ጋራዥ ግቢ ውስጥ 2ኛፎቅ ቢሮ ቁጥር 211 በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት አንድ ዋና /Original የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ፣ አንድ ቅጂ /Copy/የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ እንዲሁም፣ ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በሰም የታሸገ መሆን አለበት፡፡ በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ብር100,000.00 (አንድ መቶ ሺ) የባንክ ክፍያ ማዘዣ/C.P.O/ብቻ ለሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች ያዘጋጁትን የጨረታ ሰነድ እስከ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 211 ማስገባት ይችላሉ፣ ጨረታው በዚሁ ቀን ሐምሌ 21 ቀን 2018ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 211 የሚከፈት ይሆናል።
6. ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ያልተከሉ ተጫራቾች ወዲያውኑ ከጨረታ ውድድሩ የሚሰረዙ መሆኑን እንገልጻለን።
7. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0968135675 ወይም 0968271291 መጠቀም ይችላሉ።
8. ሕዳሴ ቴሌኮም ኢማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-07-28
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-07-28 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Hidase Telecom Share Company
- Bid bond: 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published: Jul 05, 2026
- Posted at: 2026-07-06T12:56:56.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.