መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሰነድ ቁጥር 127

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። 

ቁሳቁሶቹም፣

  1. የመኪና መለዋወጫዎች
  2. ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  3. የመዋኛ ልብሶች
  4. የተነቃቀሉ ጣውላዎች
  5. ቋሚ የመብራት ፖል (ምሰሶዎች)ለ3ኛ ጊዜ
  6. አሮጌ ጎማዎች ናቸው።
  7. ክፍልፋይ ያለው የምግብ ሳህን( ስቲልነስ ስቲል)

በመሆኑም ተወዳድሮ መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03፣ (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም፣ ከጠበል መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን ፊት ለፊት) በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ቁሳቁሶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ በማዕከሉ የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ድረስ በመምጣት ብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ። የጨረታ ሰነዱ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ቁሳቁሶች ዝርዝር የያዘ ሲሆን ዕቃዎቹን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ በሰነዱ በእያንዳንዱ ቁጥር አንፃር የተለዩትን ዕቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት እና ዕቃውን ለመግዛት ያስገቡትን ዋጋ 10% ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ጋር በማያያዝ ካሸጉ በኋላ የጠቅላላ አገልግሎት ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን 11ኛው ቀን እሁድ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

ማሳሰቢያ//

ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 30-79-64-13 ወይንም 09 75-26-41 59 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር


Tender details

  • Deadline: 2026-07-17
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-17 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ5፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Mekedonia Charity Association
  • Buyer TIN: 0027054421
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/
  • Published: Jul 07, 2026
  • Posted at: 2026-07-07T07:45:08.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders