የባሌ ትራንስፖርት፣ ከብት፣ ንግድ እና ልማት አክስዮን ማህበር 61 ሰው የሚጭን ፊያት N3 ዘመኑ ያለፈበት ለረጅም ዓመታት የቆመ ለመለዋወጫ አገልግሎት የሚውል አውቶቡስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የባሌ ትራንስፖርት፣ ከብት፣ ንግድ እና ልማት አክስዮን ማህበር (በመጣራት ላይ ያለ) ህዳር 02 ቀን 1957 ዓ.ም. የተቋቋመ ቢሆንም ማህበሩ ከ1966 ዓ.ም. ጀምሮ በንግድ ስራ ላይ አለመኖሩን ሰነዶች ያመለክታሉ። በአባላቱ ለፍርድ ቤት በቀረበ አቤቱታ ማህበሩን እንደገና ለማደራጀት ያልተቻለ በመሆኑ ሁኔታውን ለአባላቱ ቀርቦ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በተደረገ መደበኛ እና አስቸኳይ የአባላት ስብሰባ በአባላቱ አብላጫ ድምጽ ማህበሩ እንዲፈርስ ተወስኗል።

በዚህም መሰረት የማህበሩ ሂሳብ የማጣራት ስራ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል። በሂሳብ ማጣራቱ ሂደትም ከማህበሩ አባላት በቀረበ ጥያቄ መሰረት የባሌ ትራንስፖርት፣ ከብት፣ ንግድ እና ልማት አክስዮን ማህበር ንብረት የሆነ 61 ሰው የሚጭን ፊያት N3 ዘመኑ ያለፈበት ለረጅም ዓመታት የቆመ ለመለዋወጫ አገልግሎት የሚውል አውቶቡስ በባሌ ጎባ ከተማ በሐጂ መሀመድ አህመድ ሳላህ ግቢ ይገኛል። በመሆኑም ይህን ንብረት ባለበት ሁኔታ ማህበሩ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፤ በመሆኑም ከላይ የተዘረዘረውን ንብረት ለመግዛት የሚፈልግ የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 በባሌ ትራንስፖርት፤ ከብት፤ ንግድ እና ልማት አክስዮን ማህበር ስም በተከፈተው አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 01322240761900 ገቢ በማድረግ አ.አ. ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ከማህበሩ ቢሮ ኬኬር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 በመግዛት በጨረታው መሳተፍ ይችላል፤

1) ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በራሱ ወጪ ባሌ ጎባ ከተማ በሐጂ መሀመድ አህመድ ሳላህ ግቢ በመገኘት መመልከት የሚችል፤

2) በጨረታው ለመሳተፍ ብር 50000.00 የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይንም በማህበሩ ስም የባሌ ትራንስፖርት፤ ከብት፤ ንግድ እና ልማት አክስዮን ማህበር በተከፈተው አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 01322240761900 ገቢ በማድረግ ማስያዝ የሚችል፤

3) በጨረታው አሸናፊ የሆነ ማንኛውም ግለሰብ/ ድርጅት በ05 (አምስት) ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያውን በመክፈል ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በአሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ በራሱ ወጪ እና ኃላፊነት ማንሳት የሚችል፤

4) በጨረታ ሰነዱ መሰረት የሚገዛበትን ዋጋ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. ወይንም ባንክ ገቢ የተደረገበትን የባንክ ሰነድ በአንድ ላይ በማሸግ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን አ.አ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ኬኬር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 በመገኘት ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ21 (ሃያ አንድ) ቀናት ውስጥ ማስገባት የሚችል፤

5) ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣ ቀን ጀምሮ ለ21 ቀናት ክፍት ሆኖ በ21ኛው ቀን ከቀኑ በ06፡00 ሰዓት የሚዘጋ ይሆናል። ጨረታው በቀጣዩ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አ.አ. ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ኬኬር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 ይከፈታል።

6) ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

7) ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 531 3167 /09 11 12 72 65 (አቶ ዘሪሁን ደጀኔ) ወይንም 09 11 67 99 69 (አቶ ንጉሴ) በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል።

ዘመድሁን አዳነ ሰርቲፋይድ ኦዲት ድርጅት

የባሌ ትራንስፖርት፣ ከብት፣ ንግድ እና ልማት አክስዮን ማህበር (በመጣራት ላይ ያለ) ሂሳብ አጣሪ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-27
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣ ቀን ጀምሮ ለ21 ቀናት ክፍት ሆኖ በ21ኛው ቀን ከቀኑ በ6፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-28 09:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣ ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከቀኑ በ6፡00 ሰዓት የሚዘጋ ሆኖ በቀጣዩ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የባሌ ትራንስፖርት፤ ከብት፤ ንግድ እና ልማት አክሲዮን ማህበር
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: Jul 07, 2026
  • Posted at: 2026-07-07T07:55:34.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders