በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ለ2018 ዓ.ም. በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የአይሲቲ ዕቃዎች፣ ቋሚ ዕቃ እና የላውንደሪ ማሽን የሚያቀርቡለትና የሚሰሩለት ድርጅቶች ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል
- ሎት 1) የአይሲቲ ዕቃዎች
- ሎት 2) ቋሚ ዕቃ
- ሎት 3) የላውንደሪ ማሽን የሚያቀርቡለትና የሚሰሩለት ድርጅቶች ይፈልጋል
በመሆኑም
ከላይ ለተጠቀሰው የሚቀርቡ ተጫራቾች ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
1.ከሚያቀርቡት እቃ ጋር የተዛመደ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የዘመኑ ግብር የከፈሉ፧ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN፤ የVAT ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገለፅ ማስረጃ በግልፅ የሚታይ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ) በመክፈል ሰነዱን ሆስፒታሉ ግቢ በሚገኘው የመንግስት ሂሳብ እና ክፍያ ደጋፊ የስራ ሂደት በመምጣት መግዛትይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋውን ሞልተው ሲመልሱ ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ
- ሎት)1 ለአይሲቲ ዕቃዎች ብር 30,000.00(ሰላሳ ሺህ ) በጥሬ ገንዘብ፡ በሲፒኦና የባንክ ዋስትና
- ሎት 2) ለቋሚ ዕቃ ብር 10,000.00(አስር ሺህ ) በጥሬ ገንዘብ፡ በሲፒኦና የባንክ ዋስትና
- ሎት 3) ለላውንደሪ ማሽን ብር 10,000.00(አስር ሺህ )በጥሬ ገንዘብ፡ በሲፒኦና የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመግለጽ አንድ ኦሪጅናል ፋይናንሻል፤አንድ ኦሪጅናልቴክኒካል አንድ ኮፒ ፋይናንሻል፧ አንድ ኮፒ ቴክኒካል በታሸገ ኢንቬሎፕ አድርገው ሆስፒታሉ ባዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ማስገባት ይኖርባቸዋል። ተጫራቹ ወደ ጨረታው ሳጥን ፖስታውን ሲያስገባ ቴክኒካል ለብቻ ፋይናንሻል ለብቻ መሆን አለበት። ይህ ሳይሆን ቢቀር እና ተጫራቹ ፋይናንሻሉ እና ቴክኒካሉን በአንድ ፖስታ ካስገባ ጨረታዉ ወዲያውን ወድቅ ይሆንበታል።
4. ጨረታው በሚያበቃበት የመጨረሻቀን በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ በ4:30 በሆስፒታሉ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
5. የበለጠ ማስረጃ ቢያስፈልግዎት በስልክቁጥር 011 525 6823 ደውለው ይጠይቁ።
6. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-07-18
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-07-18 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ በ4:30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Gandi Memorial Hospital
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: Jul 07, 2026
- Posted at: 2026-07-07T08:09:03.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.