ድጋሚ የወጣ የቤት እና ይዞታ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍባለመብት አቶ አድማሱ በላይ እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ማዕረግ ወርቁ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር በኮ/መ/ቁ 27592 በቀን 24/10/2016 ዓ.ም እና በ23/11/2016 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ 319757 በቀን 13/02/2017 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ 319757 በቀን 29/03/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 1 የቤ.ቁ አዲስ ቤቱን የሚያዋስኑት አዋሳኞች በስተሰሜን በኩል መንገድ በስተ ደቡብ በኩል የአቶ ሙሰማ አባተ ሀሰን በስተ ምዕራብ የአቶ ብርሀኑ ምግባሩ በስተምስራቅ የአቶ ይመኑ ስቅይበሉ መኖሪያ ቤት የሚያዋስኑትን ቤት እና ይዞታ የቦታው ስፋት 45 ካ.ሜ የሆነው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 4,412,900,00 (አራት ሚሊዬን አራት መቶ አስራ ሁለት ሺ ዘጠኝ መቶ ብር ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ለሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ319757 በቀን 11/10/2018ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት 1/4ኛ 1,103,225 (አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ሃያ አምስት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት /ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-10
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-08-10 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Jul 07, 2026
- Posted at: 2026-07-07T08:16:49.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.