የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት እነ አቶ ምንዳ አስራት እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ተድባብ አበበ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.184148 በቀን 27/07/2015 ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.188754 በቀን 07/9/2015 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ.188754 በቀን 09/07/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 የቤት ቁጥር አዲስ የሆነ መኖሪያ ቤት 1ኛ ጣልቃ ገብ እና 2ኛ ጣልቃ ገብ ከሰሩት የግል ቤት ውስጥ ያለው የይዞታ ስፋት በካርታቸው 356 ካ/ሜ ከፕላን አንጻር ሲረጋገጥ ከአጠቃላይ ይዞታ ላይ ተግባራዊ የሆነ 109 ካ/ሜ የሚቀነስ ቤቱ ለመኖሪያ የሚያገለግል ሲሆን አሁን ባለው ለድርጅት እያገለገለ ያለ 1ኛ ጣልቃ ገብ እና 2ኛ ጣልቃ ገብ ከሠሩት የግል ቤት ውጭ ያለው የውርስ ቤት ብቻ ቤቱና ቦታ በተመለከተ እስከ 2014 ዓ.ም በጀት ዓመት ግብር የተከፈለ ሲሆን የ2015 ዓ.ም. በጀት አመት በአዲሱ ተመን አስተምኖ የሚከለል ሲሆን ይዞታ በባዩ ወ/ጻዲቅ ስም ተመዝግቦ ይገኛል የሐራጅ መነሻ 15,274,847.40 (አስራ አምስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰባ አራት ሺህ ስምንት መቶ አርባ ሰባት ከ40/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል። ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.188754 በቀን 30/08/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ድጋሚ ሐራጅ ሆኖ 1/4ኛ 3,818,711,85 (ሶስት ሚሊዮን ስምንት መቶ አስራ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ አስራ አንድ ከ85/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-07
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-08-07 14:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jul 08, 2026
  • Posted at: 2026-07-08T08:04:23.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders