የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በሚያስተዳድረው በቁጥር አንድ ሕንጻ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ፎቅ የሚገኘውን ቦታ ለተለያዩ ሕጋዊ አገልግሎቶች ለቢሮ፣ ለባንክ፣ ለትምህርት ተቋማት፣ ለድርጅቶች እና ለመሳሰሉት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በሚያስተዳድረው በቁጥር አንድ ሕንጻ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ፎቅ የሚገኘውን ቦታ ለተለያዩ ሕጋዊ አገልግሎቶች ለቢሮ፣ ለባንክ፣ ለትምህርት ተቋማት፣ ለድርጅቶች እና ለመሳሰሉት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ሕጋዊ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የቫት (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ CPO 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/ ብር በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ስም ማዘጋጀት የሚችሉ ሲሆን የሚያቀርቡት ሰነድ ስርዝ ድልዝ የማይነበብ ከሆነ ከጨረታ ውጭ የሚያደርግ በመሆኑ ሙሉ አድራሻና የሚከራዩበት የዋጋ ዝርዝር ግልፅ ሆኖ መቅረብ ይኖርበታል።

3. ለመከራየት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 /ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ከዩኒቨርሲቲው ገንዘብ ቤት 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 010 የጨረታውን መመሪያና ሰነድ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺ ብር ብቻ/ ከፍሎ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ 2ኛ ፎቅ በሚገኘው በዩኒቨርሲቲው ሕንጻ አስተዳደር ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሰነድ ማስገባት ይቻላል።

4. ቦታው በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱንና የዩኒቨርሲቲውን ክብር፣ ሥነ-ምግባርና ደኅንነት የማይጋፋ የሥራ ዘርፍ ያላቸው (ለሃይማኖታዊና የሥነ-ምግባር እሴቶች ተገዢ የሆኑ)።

5. የቤቱ የካሬ ሜትር መጠን እና የጨረታ የመነሻ ዋጋ ዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።

6. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ +251 11 123 3529፣ +251 91 058 6066 እና 011 181 21605 ወይም በዩኒቨርሲቲው ሕንጻ አስተዳደር ቢሮ በአካል ቀርበው ይጠይቁ

ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-15
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 /ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-07-15 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: St. Silase University
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
  • Published: Jul 08, 2026
  • Posted at: 2026-07-08T08:52:45.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders