ፀደይ ባንክ አ.ማ. የመኖሪያ ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ለመጀመርያ ጊዜ የወጣ የኃራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ፀደይ ባንክ አ.ማ አቶ ለማ ተፈራ ሶሪ ለሰጠዉ ብድር መያዣ የያዘዉን በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ የካርታ ቁጥር OR003075014013 በአቶ ጌታሁን ወዳይ ደረስ ተመዝግቦ የሚገኘዉን የመኖሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
በመሆኑም ተጫራቾች ለጫረታ ከመቅረባቸዉ በፊት የሚከተሉትን ደንቦች በመገንዘብ መጫረት እንዲችሉ ይጋብዛል።
1. የቤቱ የጫረታ መነሻ ዋጋ ብር 4,609,650.62 /አራት ሚሊዮን ስድስት መቶ ዘጠኝ ሽህ ስድትስ መቶ ሃምሳ ብር 62/100/
2. ተጫራቾች የቤቱን ጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 1/4 (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ) በጸደይ ባንክ አማ ስም በማሰራት ለጫረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
3. የጫረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠዉ የጫረታዉ ዉጤት በሚመለከተዉ አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠዉ ብቻ ይሆናል።
4. በጫረታዉ የሚሳተፈዉ በህግ ሰዉነት ያገኘ ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደምብ፤ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ዉክልና ማቅረብ አለበት።
5. የጫረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ዉስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጫረታ ያሸነፈዉን ንበረት መረከብ ይኖርበታል:: አሸናፊዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታዉ ተሰርዞ ለጨራታ ማስከበሪያ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
6 በጨረታዉ ለተሸነፉ ተጫራጮች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
7. የጫረታ አሸናፊዉ ከሚገዛዉ ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከቤቱ ጋር የተያያዙ ማናቸዉም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፡ ግብር፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% ከስም ዝዉዉሩ ጋር የሚገናኙ ማንኛዉንም ወጭዎች ገዢ ይሸፍናል/ ይከፍላል:: ዉዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረዉና የክፍያ ጊዜዉ ላልደረሰ የሊዝ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር እንዲዋዋልይደረጋል።
8. ተጫራቾች ቤቱን /ድርጅቱን/ በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ።
9. ጨረታዉ የሚካሄደዉ ሀምሌ 28/2018 ከጠዋቱ 3.00---5.00 የተጫራቾች ምዝገባ ከ5.00 እስከ ቀኑ 6.00 ሰዓት ጫረታ በኦሮሚያ ክልል ጨለለቃ ክ/ከተማ ቢሾፍቱ ሆዳነቢይ ህንፃ ይሆናል።
10.ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጫረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠተበቀ ነዉ።
- ለተጨማሪ መረጃ፡- ፀደይ ባንክ ቢሾፍቱ ቅርንጫፍ በስ.ቁ 01143303062 / 0912292609 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል።
Tender details
- Deadline: 2026-08-04
- Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Published: Jul 08, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.