የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች የግልፅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች የግልፅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፦ DIS 01/2018

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ በድርጅቱ ቃሊቲ ትራኪንግ ቅርንጫፍ፤ በሚሌ የከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ጥገና ማዕከል እና በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል አገልግለው የተመለሱ ንብረቶችን ማለትም በድርጅቱ ቃሊቲ ትራኪንግ ቅርንጫፍ እና በሚሌ የከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ጥገና ማዕከል የሚገኙ የከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ጎማዎችን እና አገልግለው የተመለሱ የመኪና ባትሪዎችን እንዲሁም በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል አገልግለው የተመለሱ የወደብ መገልገያ ማሽነሪ ጎማዎችን፤ በዋናው መስሪያቤት የሚገኙ የተነቀሉ ቴምበርድ መስታወቶችን፤ በቃሊቲ የሚገኙ የተነቀሉ ኮርኒሶችን፤ የተነቀሉ የኤሌክትሪክ ማቀፊያዎች፤ የተነቀሉ አልሙኒየም በሮችን፤ የተነቀሉ የእንጨት በሮችን፤ የተላቀቁ የእንጨት ሼልፎችን፤ ንቃይ ሴራሚኮች፤ ንቃይ ግራናይቶችን እና ንቃይ መጋረጃዎች ቁርጥራጭ አልሙኒየሞችን እና ብረታ ብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታ ሂደቱ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅት/ግለሰብ

1. የንግድ ምዝገባ፤ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርበታል።

2. ያገለገሉ ጎማዎች እና ባትሪዎች ጨረታ ላይ መጫረት የሚፈልግ ተጫራች ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶች ከአካባቢ ጥበቃ አኳያ በዘርፉ ለተሰማሩ እና ከሚመለከተው የአካባቢ ጥበቃ ወይም ከሚመለከተው የከተማ አስተዳደር/ ክልል አካባቢን ሳይበክል መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውል ስለመሆኑ ፍቃድ ያለው ወይም የፅሁፍ የሰነድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል።

3. በተጨማሪም በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የተመለከቱትን አስገዳጅ ዝርዝር መመዘኛዎችን ማሟላት የሚችል ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ረቡዕ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ጨረታው እስከ ሚታሸግበት ዓርብ ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ብቻ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ለገሀር ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 3ኛ ፎቅ በመክፈል ሰነዱን ከ6ኛ ፎቅ መውሰድና በጨረታ ሂደቱ መሳተፍ ይቻላል።

ለጨረታ የቀረቡ ንብረቶችን መመልከት የሚፈልጉ ተጫራቾች ንብረቶቹን በዋናው መስሪያ ቤት፤ በቃሊቲ ትራኪንግ፤ በቃሊቲ መጋዘን፤ በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል እና በሚሌ የጥገና ማዕከል ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት እና ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ሰነድ የገዙበትን ማስረጃ በማሳየት መመልከት ይችላሉ።

ጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ረቡዕ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የጨረታ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት ዓርብ ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከ8፡00 ሰዓት በፊት በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት አዲሱ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በመቅረብ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ሰነዱን በፖስታ ወይም በኤንቨሎፕ ውስጥ በማሸግ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከሰዓት 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ እለት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልፅ ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ ተቋሙ ጨረታውን ከመከፈት አይታገድም።

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስለ ጨረታው ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 554 9304/ 09 06 32 90 86 ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል።

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-17
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-07-17 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Shipping and Logistics Services Enterprise
  • Buyer address: ሳሪስ አቦ ቤተክርስቲያን አጠገብ ያለው የጉምሩክ ግቢ/ የቀላል ባቡር ግቢ አጠገብ የድሮ ኮሜት ግቢ ውስጥ
  • Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
  • Published: Jul 09, 2026
  • Posted at: 2026-07-09T07:22:38.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders