የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የንግድ ድርጅት ቤቶችን ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል
Description
የ16ኛ ዙር የንግድ /ድርጅት ቤቶች ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ፌቤ.ኮ/ብ/ግ.ጨ/አገ/12/11/2018
1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ስር የሚገኙ የንግድ ድርጅት ቤቶችን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ ብ.ግ.ጨ/አገ/12/11/2018 ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
2. ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የንግድ/ ድርጅት ቤቶች ኪራይ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የመወዳደሪያ የኪራይ ተመን ዋጋ በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መመሪያ መሰረት ነው።
4. ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች የተሟላ የጨረታ ሰነዱን ሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ 2፡00 እስከ 11፡00) ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ድረስ የማይመለስ ብር 1000 አንድ ሺህ ብር በካሽ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50000/ ሃምሳ ሺህ ብር/ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ሲ.ፒ.ኦ በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ስነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ክፍል 1 ላይ በተገለፀበት ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ በኮርፖሬሽኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የሚከናወን ይሆናል።
6. ተጫራቾች የንግድ ቤቶቹን በአካል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ማብቂያው ቀን ድረስ . በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ቤቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ድረስ በመቅረብና ለዚሁ ስራ በሚመደቡ ባለሙያዎች እና በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ቤቶቹን መመልከት ይችላሉ።
7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 09-10-48-59-48 ወይም 0922-98-76-33 ወይም 0922-49-18-85 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ዌብሳይት/ website www.fhc.gov.et
የፖ.ሣ.ቁ. PO Box 299
ፋክስ ቁጥር፡ 011-5-54-60-45/ 011-5-52-46-46
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-07-21
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-07-21 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Housing Corporation
- Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
- Published: Jul 10, 2026
- Posted at: 2026-07-10T07:20:46.000Z
- Buyer website: https://www.fhc.gov.et
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.