በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር የፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር የፋይናንስ ጽ/ቤት በጨረታ ማስታወቂያ:- መለያ ቁጥር፡ - 01/የ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ጥቅል ግዥ ለመፈጸም ከዚህ በታች ባሉት በምድብ የቀረቡትን ሎት1.ልዩልዩ አላቂ የቢሮ እቃዎች ግዥ፤ሎት2.ልዩ ልዩ አላቂ የጽህፍት መሳሪያዎች ግዥ፤ሎት3.ልዩልዩ አላቂ የጽዳት እቃዎች ግዥ፤ሎት4.የደንብ ልብስ ዕቃዎች ግዥ፣ሎት5ቋሚ እቃዎች ግዥ፤ሎት6.የተለያዩ ህትመቶች ግዥ፤ሎት7.የተለያዩ መስተንግዶ እቃዎች ግዥ፤ሎት8.የቄብ ዶሮ የ90 ቀን ግዥ፤ሎት9የዶሮ ኬጂ ከእንጨት የሚሰራ ግዥ፤ሎት10. የተለያዩ አትክልት ዘሮች ግዥ፤ሎት11.የህዝብ ትራንስፖርት መኪና ክራይ ግዥ እና ሎት12.ቋሚ እቃ ጥገና ከነመለዋወጫ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በጋዜጣ አምዳችሁ ላይ እንዲታወጡልን በአክብሮት እንጠይቃለን።

ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ምድብ /ሎት የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ

  • ሎት 1. ልዩልዩ አላቂ የቢሮ እቃዎች ግዥ 1%
  • ሎት2. ልዩ ልዩ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ 1%
  • ሎት3.ልዩልዩ አላቂ የጽዳት እቃ ግዥ 1%
  • ሎት4. የደንብ ልብስ ዕቃዎች ግዥ 1%
  • ሎት5. ቋሚ እቃ ግዥ 1%
  • ሎት6. የተለያዩ ህትመቶች ግዥ 5000 ብር
  • ሎት7. የተለያዩ መስተንግዶ እቃዎች ግዥ 3000 ብር
  • ሎት8. የቄብ ዶሮ የ90 ቀን ግዥ 6000 ብር
  • ሎት9. የዶሮ ኬጂ ከእንጨት የሚሰራ ግዥ 4000 ብር
  • ሎት10. የተለያዩ አትክልት ዘሮች ግዥ 3000 ብር
  • ሎት11. የህዝብ ትራንስፖርት መኪና ክራይ ግዥ 5000 ብር
  • ሎት12. ቋሚ እቃ ጥገና ከነመለዋወጫ ግዥ 6000 ብር

ሲሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የግዥ መመሪያ መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

2. ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስተር ባወጣው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውሰጥ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ።

3. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/ ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክሰ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ።

ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የክፍያ ማስያዣ/CPO/ማቅረብ የምትችሉ።

የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናል በተጨማሪ ኮፒ ማቅረብ ግዴታ ነው፡

4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሰነድ በየሎቱ የማይመለሰ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የሰራ ቀናት ውስጥ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውሰጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልቶና በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ፈርሞና ህጋዊ ማህተም አድርጎ የማያቀርብ ተጫራቶች ተቀባይነት አይኖረውም።

6. ጨረታዉ በ10ኛው የስራ ቀን በ11፡00 ሰዓት ታሸጎ በሚቀጥለው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል።ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል።

7. ተጫራቾች ናሙና እንዲያቀርቡ በተጠየቁባቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ሲኖርባቸው ናሙና ያላቀረቡ ተጫራቶች /ተወዳዳሪ/ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።

8. አሸናፊ ተጫራቾች ውል ለመፋራረም ያሸነፉበትን ዋጋ 10%/አሰር ፐርሰንት/ ውል ማሰከበሪያ ማሰያዝ ይኖርባቸዋል።

9. ወረዳው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ጥቃቅን ከሆኑ ድርጅቶች አምራች ከሆኑ ብቻው ምንቀበለው።

11. ሳንፕል ሲያመጡ በመዳበሪያ ካልመጡ ተቀባይነት የለም።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-5-57-83-69

አድራሻችን ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወሰደው መንገድ ከገነት ሆቴል በታችኛው በኩል ትንሽ ወደ ውሰጥ ገባ ብሎ ቂርቆሰ ጤና ጣቢያ ጀርባ እንገኛለን።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር የፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-23
  • Publishing entity: Kikos Sub City Woreda 11 Administration Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር በየሎቱ
  • Published: Jul 12, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders