የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ተጫራቾችን አወዳድሮ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2019
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ተጫራቾችን አወዳድሮ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት1. የፅዳት እቃዎች ፤ ሎት2. የደንብ ልብስ ፣ ሎት3. አላቂ የቢሮና የጽህፈት እቃዎች፤ ሎት4. ቋሚ ዕቃ (የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች) ሎት5.የቄብ ዶሮ፤ የዶሮ ኬጂ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት መኪና ኪራይ፣ ሎት6. ሌሎች የአይቲ ዕቃዎች፤ ሎት 7 የህትመት አገልግሎት፣ ሎት8. የመኪና ዕቃዎች ሎት9. የካፍቴሪያ አገልግሎት፣ ሎት10. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ፣ ሎት11. የልብስ ስፌት አገልግሎት
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ተጋብዘዋል።
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸዉ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
2. በአቅራቢነት ዝርዝር ዉስጥ ተመዝጋቢ የሆኑ።
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸዉ እና ተጨማሪ እሴት ታክሰ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
4. የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የሚገልፅ ክሪላንስ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
5. አሸናፊ ተጫራቾች ዉል ሲፈርሙ ዉል ማሰከበሪያ 10% በባንክ በተመሰከረ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታ ማስከበሪያ ብር ዋጋ ማለትም፡-ሎት1. 15,000.00፤ ሎት2. 25,000.00፤ ሎት3. 30,000.00፤ ሎት4. 2,000.00፤ ሎት5. 2,000.00 ሎት6. 2,000.00 ሎት7. 2,000.00 ፣ ሎት8. 2,000.00 ሲፒ.ኦ ማስያዝ አለባቸዉ።
7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የመጫረቻ ሰነድ የቴክኒክና የፋይናንስ ኦርጅናል አና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉባቸዉን እቃዎች በራሳቸዉ ትራንስፖርት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ፋይናንስ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር(10) ተከታታይ የስራ ቀናት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከደምበል የገበያ ማዕከል ጀርባ ወደ ጋዜቦ አደባባይ በሚወስደዉ መንገድ ደንበል ፖሊስ ጣቢያ አጠገብ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 05 በመቅረብ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ። እንዲሁም የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10. ጨረታዉ በ11ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የቂ/ክ/ከ/ወረዳ 09 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 05 ይከፈታል። ሆኖም የተጫራቾች አለመግገኘት ጨረታዉን ከመከፈት አያግደውም።
11. ዘግይቶ የደረሰ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም።
12. ከገዙት የጨረታ ሰነድ ዉጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ዋጋ የለዉም።
13. ተጫራቾች ለሎት1፣ ለሎት 2፣ ለሎት3፣ ለሎት6፣ ለሎት7፣ ለሎት8 ላሉ እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
14. ጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች በራሳችሁ ያመረታችሁት እቃ/ ንብረት ካልሆነ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
15. የጨረታ መክፍቻዉ ቀን በዓል ወይንም እሁድ አና ቅደሜ የሚዉል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተጠቀሰዉ ስዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
16. ፅ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
ለበለጠ መረጃ አድራሻ፡- ከደምበል የገበያ ማዕከል ጀርባ ወደ ጋዜቦ አደባባይ በሚወስደዉ መንገድ ደንበል ፖሊስ ጣቢያ አጠገብ
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 09 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር፡- 011 557 4677
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-24
- Publishing entity: Kirkos Sub City Woreda 09 Administration Finance and Development Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jul 13, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.