ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር የሰራተኛ ሰርቪስ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ኢትዮ አግሪ-ሴፍት ኃላ. የተ. የግ. ማኅበር
የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር EAC 037/2018
1. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር የሰራተኛ ሰርቪስ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ድረስ “ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ” ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎር አግሮኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ አግሪ ሴፍት ሕንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያቁጥር ያላቸው፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት፡-
- አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሽገ ፖስታ
- አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በታሽገ ፖስታ እንዲሁም፣
- ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት።
- በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች የሰራተኛ ሰርቪስ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥን የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 208 ሲሆን፣ ጨረታውን የመክፈቻ ቀን ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ 4:45 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 የሚከፈት ይሆናል።
6. ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን።
7. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0116676204 ፋክስ ቁጥር 0116732006 መጠቀም ይችላሉ።
8. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-07-21
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-07-21 10:45
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethio Agri-CEFT Pvt.Ltd.Co.
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jul 13, 2026
- Posted at: 2026-07-13T11:54:14.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.