ቤንቬኑቲ ወንድማማቾች ኃ/የተ/የግ/ማ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳደሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ መኪኖች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ቤንቬኑቲ ወንድማማቾች ኃ/የተ/የግ/ማ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳደሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተሸከርካሪዎቹን ለመግዛት የምትፈለጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘሩ መስፈርቶች መሰረት ጨረታው ላይ እድትሳተፉ እናሳውቃለን። የጨረታ መስፈርቶች፡-
1) ማንኛውም ተጫራች ለቀረበው ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበትን 10% አስር በመቶ/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ቤንቬኑቲ ወንድማማቾች ኃ/የተ/የግ/ማ በሚል ማስያዝ አለባቸው።
2) ተጫራቾች ሕጋዊና የታደሰ የ2018 ዓ/ም ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ ቢሆኑ ይመረጣል።
3) ለጨረታ ሠነድ ጠመንጃ ያዥ ባንክ /ቴሌ ገራዥ/ ፊት ለፊት በሚገኘው ቤንቬኑቲ ወንድማማቾች ኃ/የተ/የግ/ማ እህት ኩባንያ ኦሜዳድ ኃ/የተ/የግ/ማ የኋላ ወርቅ ህንፃ በመገኘት 200 ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
4) ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውን ፊርማቸውንና የመታወቂያ ኮፒ አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።
5) ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ 100% እና 15% ተ/እ/ታክስ ያካተተና የሚያቀርቡትም ዋጋ በኢትዮጵያ ብር መሆን ይኖርበታል።
6) ተጫራቾች ዋጋ ለመሙላት በተዘጋጀው ዝርዝር ቅፅ ላይ ብቻ መጠቀም ይኖርባቸዋል።
7) ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም።
8) የተሸከርካሪዎቹን ዝርዝር ሁኔታ በአካል ለማየት ከፈለጉ በቅሎ ቤት ቴሌ ጋራዥ ፊት ለፊት በሚገኘው የመኪና ማቆሚያ እና ዱከም መጋዘን ውስጥ ከሰኞ አስከ ዓርብ ከጠዋቱ 3፡00-10፡00 ድረስ ማየት ትችላላችሁ።
9) አሸናፊው ተጫራች በ15 የስራ ቀናት ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ማንሳት ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ባያነሳ ያስያዘው ሲፒኦ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል። ከአሸናፊነት ተሰርዞ ድርጅቱ የራሱን አዋጪ መንገድ በመጠቀም መኪናዎቹን የመሸጥ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።
10) ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11) ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች ለመንግስት የሚከፈል ማንኛውም የስም ማዛወሪያ ወጪ ይከፍላል።
12) ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት ተጫራቾችድርጅቱ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ በመሙላት ዋና ሰነድ /Bid document/ የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ በድርጅቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በ16ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- ስ.ቁጥር-09 11 67 85 67 / 09 66 25 71 46/ 09 21 79 71 81/ 09 30 03 34 41
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ቤንቬኑቲ ወንድማማቾች ኃ/የተ/የግ/ማ
Tender details
- Deadline: 2026-07-30
- Publishing entity: ቤንቬኑቲ ወንድማማቾች ኃ/የተ/የግ/ማ
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jul 14, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.