በቂ/ክ/ከ/ት/ጽ/ቤት የጥበብ ገበያ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2019 የበጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድረን መግዛት እንፈልጋለን
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በቂ/ክ/ከ/ት/ጽ/ቤት የጥበብ ገበያ ቅድመ አንደኛ ፣አንደኛ እና የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2019 የበጀት ዓመት
- የሰራተኞች የደንብ ልብስ
- አላቂ የቢሮ እቃዎች
- አላቂ የት/ት ዕቃዎች
- የፅዳት ዕቃዎች
- ቋሚ ዕቃዎች
- ለፕላንት ለማሽነሪ መሳሪያ እድሳት ጥገና
- የህክምና እቃዎች
- የጥገና ስራዎች ከህጋዊ አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድረን መግዛት እንፈልጋለን።
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተለውን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የአገር ውስጥ ግብር አጠናቀው የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. የቫት ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
3. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
4, የጨረታ ማስከበሪያ አምስት ሺህ ብር (5,000) ከባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ የሚችል
5. የጨረታ ሰነዱን ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) የማይመለስ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በጥበብ ገበያ የመጀ/ደ/ት/ቤት በካሸር ቢሮ በግንባር በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
6. ተጫራቾች የሚጫረቱትን እቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው።
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እሰከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት 11፡30 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
8. ጨረታው የሚከፈተው በ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሲሆን በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 04 ይከፈታል።
9. የተሰረዘና የተደለዘ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይሆናል።
10. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን እቃ ዝርዝር መግለፅ አለባቸው።
11. ለተጫራቾች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ክፍያ የሚከፈላቸው እቃዎች ሙሉ በሙሉ ለት/ቤቱ ንብረት ክፍል ገቢ አድርገው ሲያጠናቅቁ ነው።
12. በጨረታው መክፈቻ ወቅት የሚከፈተው ኮፒው ስለሆነ አስፈላጊ ሰነዶችና CPO ማድረግ ያለባቸው ኮፒ ውስጥ ነው።
13. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. ተጫራቾች ሰነዱን ኮፒ እና ኦርጅናል ብለው በመለየት አያይዘው ሰነድ ኮፒው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
የጥበብ ገበያ ቅድመ አንደኛ እና የመጀ/ደ/ት/ቤት
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-470-29-21 / 011-470-29-22 / 011-416-55-42 /
አድራሻችን ፡- ወደ ቴሌ ጋራጅ በሚወስደው መንገድ አድአ ሆቴል አጠገብ 200 ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ።
በቂ/ክ/ከ/ት/ጽ/ቤት የጥበብ ገበያ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛ እና የመጀ/ደ/ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-24
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እሰከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት 11፡30
- Bid opening: 2026-07-25 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Yetibeb Gebeya Kindergarten and Elementary School
- Buyer address: ወደ ቴሌ ጋራዥ በሚወስደው መንገድ አድአ ሆቴል አጠገብ
- Bid bond: 5,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Jul 14, 2026
- Posted at: 2026-07-14T08:22:07.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.