በጉ/ክ/ከ/ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ለ2019 በጀት ዓመት በፑሉ ስር ለሚገኙ ጽ/ቤቶች የተለያዩ አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019

በጉ/ክ/ከ/ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ለ2019 በጀት ዓመት በፑሉ ስር ለሚገኙ ጽ/ቤቶች የተለያዩ አልግሎቶች በአጠቃላይ 10 ሎቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 የድንኳን ኪራይ
  • ሎት 2 ዲጄና ዲኮር ኪራይ
  • ሎት 3 የሕትመት ስራዎች
  • ሎት 4 የቦቴ ውሃ አቅርቦት
  • ሎት 5 የኮምፒውተር ጥገና
  • ሎት 6 የመኪና ኪራይ
  • ሎት 7 የካፍቴሪያ መስተንግዶ
  • ሎት 8 የከባድ መኪና ጥገና
  • ሎት 9 የቀላል መኪና ጥገና
  • ሎት 10 የጄኔሬተር ጥገና

1. ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን አድራሻቸውንና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ጨረታ ፖስታ ላይ ለየትኛው አገልግሎት እንደሚወዳደሩ በግልፅ ለይተው መጻፍ አለባቸው።

3. ተጫራቾች ድረ ገፅ (ዌብ ሳይት) ላይ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ እንዳላቸው የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም አስተዳደሩ ባወጣው ጨረታ ላይ ከውል በፊት የዕቃውን ብዛት 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል እንዲሁም ከውል በኃላ ደግሞ 25% የዋጋውን ተጨማሪ ማዘዝ ይችላል።

4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም ተጫራቾች ለተወዳደሩባቸው ሎት 3 ናሙና እና ሌሎች ላይ ማስረጃ ማስገባት አለባቸው።

5. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው አገልግሎቶች ወይም ዕቃዎች በሙሉ መስሪያ ቤቱ ቴክኒክ ኮሚቴ 15. ደረጃቸውን የጠበቁ ስለመሆናቸው ይገመግማሉ።

6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫት ያካተተ መሆኑን ወይም ዋጋው ከቫት ውጪ መሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው ይህ ባይሆን ዋጋው ቫት ያካተተ ተደርጐ ይወሰዳል።

7. ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ሎት 1 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ሎት 2 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ሎት 3 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ሎት 4 10,000 (አስር ሺህ ብር)፤ ሎት 5 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ሎት 6 10,000 (አስር ሺህ ብር) ሎት 7 50,000/ሃምሳ ሺህ ብር/ ሎት 8 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ሎት 9 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ ሎት 10 15,000/አስራ አምስት ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ በጉ/ክ/ከ/ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት ክ/ሂ ቡድን ስም በባንክ በተመሰከረ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርበታል። ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሎት ወይም ስነድ በመክፈል በመንግስት የስራ ሰዓት ጉለሌ ከፍለ ከተማ ገ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ቢሮ 6ኛ ፎቅ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

8. የጨረታ ሰነዶች በሙሉ በኢንቨሎፕ ታሽገው ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ለየብቻው በማድረግና በማያያዝ ማህተማቸውን በፖስታዎች ላይ በማኖር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

9. የካፒታል መጠናቸው ከብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በላይ የሆኑ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

10. የጨረታው ጊዜ የሚያበቃው በ10ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ታሽጐ በሚቀጥለው የስራ ቀን 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት የሚከፈት ይሆናል።

11. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

12. በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች በዚህ ጨረታ እንዲወዳደሩ እየተጋበዙ እንዱሁም ከአደራጃቸው አካል ለጨረታ ሰነድ በነፃ እንዲወስዱ፤በጨረታ ማስከበሪያ እና በውል ማስከበሪያነት የሚያገለግል በግልፅና በዝርዝር በተፃፈ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።

13. አንድ ተጫራች ሌላው ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

14. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት ጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል ይህ ባይሆን ግን ከጨረታ ይሰረዛሉ።

15. ተጫራቾች በንግድ ፍቃዳቸው በስተጀርባ ላይ የተዘረዘሩትን የንግድ ዘርፍ አይነቶች ኮፒ አድርገው ማቅረብ አለባቸው የተጫራቾች ማህተምና የንግድ ፈቃዳቸው እንዲሁም የደረሰኛቸው ስያሜ አንድ አይነት መሆን ይኖርበታል።

16. በጨረታ መወዳደሪያ የሚቀርብ ዋጋ ለአንድ አመት ፀንቶ ይቆያል።

17. ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ከመ/ቤታችን ጋር ውል ማስከበሪያ ላሸነፉባቸው እቃዎችና አገልግሎት የጠቅላላ ዋጋውን 10% ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህ ባይሆን ግን በጨረታ ያስያዙት /ሲፒኦ/ በቀጥታ ለመንግስት ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛሉ።

18. ተጫራች አሸነፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በራሱ ትራንስፖርት ወጪ መ/ቤታችን ወይም በሚፈለግበት ቦታ ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት።

19. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 812 5178 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።

በጉ/ክ/ከ/ፐ/ሰ/የሰው/ኃ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን


Tender details

  • Deadline: 2026-07-24
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-25 09:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ታሽጐ በሚቀጥለው የስራ ቀን 3፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ጉለሌ ክ/ከ/ በፐ/ሰ/የሰው/ሃ/ል/ ጽ/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ
  • Published: Jul 14, 2026
  • Posted at: 2026-07-14T08:25:28.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders