Vehicle and Machinery Sale

ኦሜዳድ ኃ/የተ/የግ/ማ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪ ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳደሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሉ ልዩ ልዩ መኪኖች ሽያጭ  የጨረታ ማስታወቂያ

ኦሜዳድ ኃ/የተ/የግ/ማ የተለያዩ ያገለገሉ የተሽከርካሪ ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾችን አወዳደሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ተሽከርካረዎቹን ለመግዛት የምትፈለጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘሩ መስፈርቶች መሰረት ጨረታው ላይ እድትሳተፍ እናሳውቃለን።

የጨረታ መስፈርቶች

1) ማንኛውም ተጫራች ለቀረበው ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበትን 10% /አስር በመቶ/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ኦሜዳድ ኃ/የተ/የግ/ማ በሚል ማስያዝ አለባቸው።

2) ተጫራቾች ሕጋዊና የታደሰ የ2018 ዓ/ም ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ ቢሆኑ ይመረጣል።

3) ለጨረታ ሠነድ ከዋናው መስሪያ ቤት ጠመንጃ ያዥ ባንክ /ቴሌ ገራዥ ፊት ለፊት በሚገኘው የኋላ ወርቅ ህንፃ በመገኘት 200 ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

4) ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውን ፊርማቸውንና | የመታወቂያ ኮፒ አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።

5) ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ 100% እና 15% ተ/እ/ታክስ ያካተተና፤ የሚያቀርቡትም ዋጋ በኢትዮጵያ ብር መሆን ይኖርበታል።

6) ተጫራቾች ዋጋ ለመሙላት በተዘጋጀው ዝርዝር ቅፅ ላይ ብቻ መጠቀም ይኖርባቸዋል።

7) ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም።

8) ተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር ሁኔታ በአካል ለማየት ከፈለጉ ዋናው መ/ቤት በቅሎ ቤት ቴሌ ጋራዝ ፊት ለፊት ካለው በቢሮችን በሚገኘው የመኪና ማቆሚያ ውስጥ ከሰኞ አስከ አርብ ከጠዋቱ 3፡ዐ0– 10፡ዐዐ ድረስ ማየት ትችላላችሁ።

9) አሸናፊው ተጫራች በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ማንሳት ይኖርበታል። በእነዚህ ቀን ውስጥ ባያነሳ ያስያዘው ሲፒኦ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል። ከአሸናፊነት ተሰርዞ ድርጅቱ የራሱን አዋጪ መንገድ በመጠቀም መኪናዎቹን የመሸጥ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።

10. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች ለመንግስት የሚከፈል ማንኛውም የስም ማዛወሪያ ወጪ ይከፍላል።

12) ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት ተጫራቾችድርጅቱ  ባዘጋጀነው ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ በመሙላት ዋና ሰነድ /Bid document/ የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ በድርጅቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፣ ጨረታው በ16ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁጥር 09 11 67 85 67/ 09 66 25 71 46/ 09 21 79 71 81/ 09 30 03 34 41

ኦሜዳድ ኃ/የተ/የግ/ማ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-28
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ
  • Bid opening: 2026-07-29 09:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ጠዋት 3፡00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Omedad PLC
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jul 14, 2026)
  • Posted at: 2026-07-14T08:59:22.000Z
← Back to all tenders