የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍባለመብት ወ/ሮ ፍሬህይወት ጣሰው እና በፍ/ባለዕዳ አቶ አዱኛ ዳኘው መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 236697 በቀን 23/7/2017 ዓ.ም እና መ/ቁ 336042 18/8/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የቤ/ቁ 1675 በሆነው ቤት ለፍ/ባለዕዳ የደረሳቸውን በተሰራው እስኬች በተ.ቁ 1 የተሰየመው የቦታ ስፋት 240 ካ.ሜ የሆነው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 7,230,250 (ሰባት ሚሊዬን ሁለት መቶ ሰላሳ ሺ ሁለት መቶ ሀምሳ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት /ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ5 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበትመሆኑን እንገልፃለን።

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-07
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jul 15, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders