የቤት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት ወ/ሮ እሌኒ ተከስተ ፀጋዬ እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ብርሃን ከበደ አየለ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ በመዝገብ ቁጥር 03533 የተሰጠውን ውሣኔ ለማስፈፀም በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 02 የሚገኘው እና ቁጥሩ መል/ሊ/3642 በሆነው የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በተመዘገበው ቦታ ላይ ያረፈው ቤት በጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 60,000,000.00 (ስልሳ ሚሊዮን ብር) እንዲሸጥ የታዘዘ በመሆኑ ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በጨረታ አወዳድሮ በሀራጅ መሸጥ አስፈልጓል። ስለሆነም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 4፡00 ድረስ ባለው ጊዜ የተጫራቾች ምዝገባ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ የሚካሔድ ሲሆን ጨረታው በተጠቀሰው ቀን እና ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ከጠዋቱ 4፡10 እስከ 5፡10 ባለው ጊዜ ይከናወናል። በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ መታወቂያ በመያዝ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፉበትን ገንዘብ 1/4ኛውን ወዲያውኑ በሞዴል 85 በፍ/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ማስያዝ አለባቸው። ቀሪውን 34ኛ ገንዘብ ደግሞ ጨረታው በተካሔደ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቀው ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ይህ ባይሆን ቀድሞ የተያዘው ገንዘብ ለጨረታ የወጣው ወጪ ተቀንሶለት ቀሪው ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን ሊገነዘቡ ይገባል።

የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የድሬዳዋ ምድብ 1ኛ ፍትሐብሔር ችሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-20
  • Publishing entity: Dire Dawa Federal First level Court
  • Published: Jul 15, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders