ቡና ባንክ አ.ማ. የመኖሪያ ቤት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ማስታወቂያ

ቁጥር፤ ቡባ/ሕአዳ/ሐራጅ/046/2018

ቡና ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁ. 97/1990 (እንደተሻሻለው) በተሰጠው ስልጣን መሠረት ቀጥሎ የቀረቡትን ንብረቶች በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የተበዳሪ ስም

የንብረት አስያዥ ስም

አበዳሪ ቅርንጫፍ

ለጨረታ የቀረበው ንብረትና የቦታ ስፋት

የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር

ጨረታው የሚከናወንበት

ጨረታው የወጣው

 

ቀን

ሰዓት

 

ለጨረታ የቀረበው ንብረት

ከተማ/ክ/ከተማ/ቀበሌ ወረዳ/ የቤት.ቁጥር

የካርታ ቁጥር

የቦታ ስፋት

 

1

አቶ ታደሰ ዳዊት ሲባኒ

ተበዳሪ

ጋምቤላ

 

የመኖሪያ ቤት

በጋምቤላ // ጋምቤላ ከተማ ቀበሌ 05

36797/15

 

411 ካ.ሜ

 

5,680,778.24

 

ነሐሴ 08 ቀን 2018 .

4:00-5:00

 

ለመጀመረያ ጊዜ

 

 

2

አቶ ሰለሞን ታደሰ አበበ

ተበዳሪ

ፒያሳ

የመኖሪያ ቤት

በባሕር ዳር ከተማ፤ ግንቦት 20 /ከተማ (በአሁኑ ዳግማዊ ምኒልክ /ከተማ

/20//ክ/5544/10

250 ካ.ሜ

5,867,895.70

 

ነሐሴ 08 ቀን 2018 .

5:00-600

ለሁለተኛ ጊዜ

 

የሐራጅ ደንቦች ፣

1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በቡና ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።

2. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ተጠቃሎ መከፈል አለበት። ካልተከፈለ የተያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል:: በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃሉ። ላላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል።

3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው:: ተበዳሪ እና ወኪሎቻቸው ባይገኙም ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።

4. የተጫራቾች ምዝገባ ከእያንዳንዱ የንብረት ሐራጅ መዝጊያ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል:: በሐራጁ የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም።

5. የሐራጁ አሸናፊ /ገዢ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብር በዋጋው ላይ የሚታሰብ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ካለ ከስም ማዛወሪያ ክፍያ ጋር የተገናኙና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው /አሸናፊው ይከፍላል።

6. በሐራጁ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ለማየት ከአበዳሪ ቅርንጫፉ ጋር በመነጋገር ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ይቻላል።

7. ተጫራቹ የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በጽሑፍ ሲደርሰው ብቻ ነው።

8. ጨረታው ንብረቶቹ በሚገኙበት በቡና ባንክ ኢማ ቅርንጫፎች የሚካሄድ ይሆናል።

9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፣ ሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ስ.ቁ 011-1-58-08-63/ 011-1-26-36-09 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።


Tender details

  • Deadline: 2026-08-14
  • Publishing entity: Bunna Bank S.C.
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jul 15, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders