የዲባዩ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት መኖሪያ ቤት መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በፍ/ለሙበት፡- ዘነበ አለማየሁ እና በፍ/ባለዕዳ ብርሃኑ ጉተማ

  1. በቢሾፍቱ ከተማ ዲባዩ ክፍለ ከተማ ቢፍቱ ወረዳ ውስጥ በ160ካሬ ሜትር መሬት ላይ ሰፍሮ የሚገኝ መኖሪያ ቤት ካርታ ቁጥሩ Bl/17491/12 በሆነው በአፈፃፀም ተከሳሽ ባለቤት በወ/ሮ መሰረት እሸቱ ስም ተመዝግቦ የሚታወቅ ግምት ብር 1,715,091.38 (አንድ ሚሊዬን ሰባት መቶ አስራ አምስት ሺህ ዘጠና አንድ ብር ከሠላሳ ስምንት ሣንቲም) ነው።
  2. የጨረታው ሽያጭ በግልጽ የሚሸጥ ሆኖ በዚህ 1ኛ ጨረታ ላይ ከተወዳዳሪዎች ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበው የሚሸጥ ይሆናል፣
  3. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ዲባዩ ክፍለ ከተማ ቢፍቱ ወረዳ በጨረታ የሚሸጥ መኖሪያ ቤት በሚገኝበት ቦታ ሆኖ ጠዋት ከ3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 6፡30 ሰዓት የሚካሄድ ይሆናል።
  4. ጨረታውን ያሸነፈው ገዥ ከገዛበት ዋጋ ውስጥ ብር 25% ወዲያው አስይዞ ቀሪውን ዋጋ በ10 ቀናት ውስጥ መክፈል አለበት፡፡
  5. ጨረታ ማስታወቂያ ለአንድ ወር ጊዜ ድረስ አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ የጨረታው ሽያጭ የሚካሄድበት ቀን 29/11/2018 ጠዋት ከ3፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት መኖሪያ ቤቱ በሚሸጥበት ቦታ ይሆናል።
  6. ማንኛውም የጨረታ ተወዳዳሪ ከጨረታው መነሻ ዋጋ ውስጥ ¼ ኛውን በCPO ማስያዝ አለበት።
  7. የጨረታ ውጤት በ30/11/2018 ለከሰዓት በፊት ለ8፡00 ሰዓት እንደሚገልፅ ፍ/ቤቱ አዟል።

የዲባዩ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ፍ/ብሔር ችሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-05
  • Publishing entity: በቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዲባዩ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jul 15, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders