በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያ እቃዎች፣ የተለያዩ አላቂ የፅዳት እቃዎች፣ የተለያዩ ቀለሞች እና የተሽከርካሪ ጎማ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ብሄራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር-001/2019

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለከተማው ሴከተር መ/ቤቶች  አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በጥቅል ግዥ ለመፈፀም በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ባላቸው አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያ እቃዎች፣
  •  ሎት-2 የተለያዩ አላቂ የፅዳት እቃዎች፣
  • ሎት-3 የተለያዩ ቀለሞች፣
  • ሎት 4 የተሽከርካሪ ጎማ

በዚህም መሰረት፡- ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ (የታክስ ክሊራንስ) ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑና ስለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። እንዲሁም የንግድ መለያ ቁጥር/TIN NUMBER/ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3.  ተጫራቾች (egp) በኦን ላየን የተመዘገባችሁ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ በወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ፤ CPO ለእያንዳንዱ ጨረታ ወይም ሎት 50,000(ሃምሳ ሺ ብር) በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከወ/ጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ግ/ን/አስ/ዋና/ስራ ሂደት ክፍል ቀርቦ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
  6. ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15/ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 የጨረታው ሳጥን ታሽጎ በዚሁ ቀን 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ሁለት ኮፒውን በተናጠል ለይቶ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. መ/ቤቱ የጨረታ አሸናፊ ተወዳዳሪ የሚለየው ተወዳዳሪዎች ለእያንዳንዱ ነጠላ እቃ ባቀረቡት ዋጋ መሰረት የቀረበ አነስተኛ ዋጋ ወይም በጥቅል ሎት በማየት የተሻለውን የጨረታ አሸናፊ የመለየት ስራ ሊሰራ ይችላል።

ማሳሰቢያ ፅ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

  • በጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታው ከመክፈት አያስተጓጉልም።
  • መ/ቤቱ ከሸጠው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ ሞልቶ መወዳደር አይቻልም።
  • የጨረታ ማስታወቂያውንና የጨረታ ሰነዱ የሚጠይቀውን ዝቅተኛ መስፈርት የማያሟሉ ተጫራቾች ወይም አቅራቢዎች ከጨረታው ውጪ ይደረጋሉ።
  • የጨረታውን መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ብሄራዊ የህዝብ በዓል ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይተላለፋል።

ለበለጠ መረጃ አድራሻ፡- በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ከብሩክ ህንፃ ፊት ለፊት ቴሌ አጠገብ ከተሰራው አዲሱ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ህንፃ ውስጥ 1ኛ ፎቅ ወደ ቀኝ ሲታጠፉ የወልቂጤ  ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0113301548/0911921780/ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-30
  • Publishing entity: Welkite City Administration Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Jul 15, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders