በአብክመ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የሰንበቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የሚውል ልዩ ልዩ ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎችን፣ የደንብ ልብስና የመኪና ጎማና እስፔር ፓርቶችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 01/2018

በአብክመ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የሰንበቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ሰንበቴ ከተማ ከአዲስ አበባ በደሴ ከተማ መስመር በ265 ኪ/ሜ ላይ የምትገኝ ሲሆን ለሰንበቴ ከተማ አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሰንበቴ ከተማ አስተዳደር ለሴክተር መሥሪያ ቤት አገልግሎት የሚውል

  • ልዩ ልዩ ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
  • የጽዳት እቃዎችን፣
  • የደንብ ልብስና
  • የመኪና ጎማና እስፔር ፓርቶችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡-

1. በዘርፉ የተሰማሩ የንግድ ፈቃድ ያላውና በዘመኑ የታደሰ መሆን አለበት።

2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /Tin no/ ያላቸው መሆን አለበት።

3. ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው መሆን አለበት።

4. ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያላቸው መሆን አለበት።

5. በጨረታ መሣተፍ የሚፈልጉ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከለ ከ/አስ/ገ/ጽ/ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 4 ከ 9/11/2018 ዓ.ም እስከ 29/11/2018 ዓም ዝርዝር ማብራሪያ ያገኛሉ።

6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው በታሸገ ፖስታ የአቅራቢው ስም እና አድራሻ የሚገልፅ ማህተም በማደረግ ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት እስከ 29/11/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ሰ/ከ/አስ/ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው በዚሁ ዕለት 8፡05 ሰዓት ይታሸግና 8፡15 ሰዓት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፤ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ በተገለፀው ሰዓት መሰረት ይከፈታል፤ በማይገኙ ተጫራቾች ምክንያት የጨረታው መክፈቻ ጊዜ አይስተጓጎልም።

7. ጨረታው ናሙና በተጠየቁባቸው ዕቃዎች በናሙናው መሰረት ብቻ ማቅረብ አለባቸው፤

8. ሁሉንም የጨረታ አይነቶች በነጠላ የጋ የምናወዳድር ሲሆን፣

9. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች የውል ማስከበሪያ 10% cpo ማስያዝ አለበት።

10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ወይም በጥሬ ገንዘብ ለመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 4 በመክፈልና ደረሰኝ በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር መቅረብ አለበት።

11. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብት አለው።

በአብክመ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የሰንበቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-05
  • Publishing entity: Senbete City Administration Finance Office
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Jul 16, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders