የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት እነ ካሳ ግርማይ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ቤትና ሪል እስቴት ኃ የተ/የግ/ማህበር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/351248 በ15/07/2018 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/351572 በ27/9/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 05 የመለያ ቁጥር AA00004051216 ቤትና ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የቦታው ስፋት 704ካ/ሜ ተነጻጸሪ ድርሻ 256 ካ/ሜ የሆነ በመዋቅራዊ ፕላኑ ለወረዳ ማዕከል አገልግሎት እንዲውል የተጠና ማለትም ለገበያ ማዕከል፣ጤና ጣቢያ ፣ ወጣት ማዕከል፣ ቤተመጻሃፍት፣ ፖሊስ ጣቢያ እና ሌሎች አስተዳደራዊ አገልግሎቶች የሚሰጥባቸው ግንባታዎችን የሚውል ቦታን የሚያመለክት ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 11,211,706 (አስራ አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ አስራ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ስድስት) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆነን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌደራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ፍ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-18
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Jul 17, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.