የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት አቶ ድልባ ድርጎ እና በፍርድ ባለእዳ ወ/ሮ ጋንቴ ኤሌሞ መካከል ስላለው አፈፃፀም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 56955 በ24/02/2012 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/109979 በ26/12/2012ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/109979 በ26/02/2013ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/125617 በ21/08/2014 ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/131258 በ12/12/2014ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 12 የቤት ቁጥር 563 የሆነውን ቤትና ይዞታ በእነ መኮንን ደላሴ ደርጎ ስም የተመዘገበ ሲሆን በካርታ ቁጥር ወ12/ውዝ/631/14931/00 በሴሪ ቁጥር 024418 የተመዘገበ የቦታው ስፋት በካርታው ጠቅላላ የግቢው ስፋት በፕሮፖርሽን 268.20 ካ.ሜ ሲሆን ቤቱ ያረፈበት 114.30ካ.ሜ በፕሮፖርሽን ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው የቦታ ስፋት 48.42 ካ.ሜ ጠቅላላ በፕሮፖርሽን ለግለሰቡ የሚደርሰው የቦታ ስፋት 162.73 ካ.ሜ የቤቱ የሽያጭ ዋጋ መነሻ ግምት ብር 3,429,900 (ሶስት ሚሊዮን አራት መቶ ሀያ ዘጠኝ ሺ ዘጠኝ መቶ ብር) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትየጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን። ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆነን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-19
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Jul 17, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.