ድጋሚ የወጣ የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት እነ ቤቴልሔም አለማየሁ እና የፍ/ባለዕዳ እነአቶእስጢፋኖስ አለማየሁ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/134215 በ22/02/2011ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ እና በኮ/መ/ቁ/187947 በ30/9/2015ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/187947 በ18/03/2016ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/187947 በ29/5/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በሰሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቤት ቁጥር 206 ሰነድ አልባ ካርታ ያልወጣለት ግን ደብተር ያለው የቦታ ስፋት 680ካ/ሜ ግንባታ ያረፈበት ቤት ስፋት 44.75 ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 21,160,920 (ሃያ አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ስልሳ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ምንም ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል። ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.187947 በቀን 19/10/2018ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ድጋሚ ሐራጅ ሆኖ 1/4ኛ 5,290,230 ( አምስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-18
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Jul 17, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.