በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የባቱ ኮስቲክ ሶዳ ፋብሪካ በፋብሪካው ዋና ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ብረታ ብረቶችን፣ አንድ ደብል ካፕ ሚትሱቢሽ ተሽከርካሪ፣ ያገለገሉ ጎማዎች፣ አንድ አዲስ የትራክተር ጎማ፣ የኬሚካል መከላከያ ሸክላዎችን፣ የወረቀት ማሸጊያ ከረጢቶችንና የብረት ዝገት መከላከያ ቀለም እና ያገለገሉ ፍሪጆችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ቁጥር 003-2018
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የባቱ ኮስቲክ ሶዳ ፋብሪካ በፋብሪካው ዋና ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ብረታ ብረቶችን፣ አንድ ደብል ካፕ ሚትሱቢሽ ተሸከርካሪ፣ ያገለገሉ ጎማዎች ፣አንድ አዲስ የትራክተር ጎማ የኬሚካል መከላከያ ሸክላዎችን፣ የወረቀት ማሸጊያ ከረጢቶችንና የብረት ዝገት መከላከያ ቀለም እና ያገለገሉ ፍሪጆችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች አሟልቶ መወዳደር ይችላል።
1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት እና ለግብር ከፋይ የሚሰጥ ሰርተፍኬት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች ባቱ ከተማ ካለው የፋብሪካው ዋና መስሪያ ቤት ወይም አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ከኩዌት ኤምባሲ 10 ሜትር ገባ ብሎ ናሚቢያ ወይንም ጅቡቲ ኤምባሲ ፊትለፊት ከሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ የማይመለስ ብር ሁለት መቶ (200.00) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላል።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድና የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ ንብረቱ የሚገኝበት ባቱ(ዝዋይ) ከተማ ፋብሪካው ቅጥር ግቢ ድረስ በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 3 በመቶ (3%) በባቱ ኮስቲክ ሶዳ ፋብሪካ ስም የተዘጋጀ የባንክ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ድርጅቱ በዚሁ ጨረታ ሰነድ ላይ ማሻሸያዎችን ካደረገ ከዋጋ ማቅረቢያው በፊት የጨረታ ሰነድ ለገዙት ተጫራቾች በሙሉ በስልክ ይገልፃል። እንዲሁም በድርጅቱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ይለጥፋል።
6. ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት/ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ6 ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ7ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ/ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ውኪሎቻቸው በተገኙበት ባቱ/ዝዋይ ከተማ የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ማርኬቲንግ ቢሮ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻው ቀን በዓል ወይንም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
7. የጨረታው አሸናፊዎች ተለይተው እንደታወቁ ያሸነፉበትን ዋጋ ቀርበው ከከፈሉ በኋላ በአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ጊዜ ውስጥ በራሳቸው ተሸከርካሪ ማንሳት ይጠበቅባቸዋል።
8. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ
አ.አ ስልክ ቁጥር 011-6-18-43-10/17 ባቱ ስልክ ቁጥር 046-441-34-15
09-27-02-47-81
09-55-88-29-73
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የባቱ ኮስቲክ ሶዳ ፋብሪካ
Tender details
- Deadline: 2026-07-23
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-07-23 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Chemical Industry Corporation
- Buyer address: ቦሌ ሩዋንዳ ናሚቢያ/ጅቡቲ ኤምባሲ ፊት ለፊት
- Bid bond: 3%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jul 17, 2026
- Posted at: 2026-07-17T08:23:33.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.