በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር የፋይናንስ ፅ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን ለመግዛት እና ለማሠራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር የፋይናንስ ፅ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለተለያዩ ፅ/ቤቶች የሚያስፈልጉትን የእስቴሽነሪ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የመኪና ጎማ እና እቃዎች እና የአገልግሎት ማለትም የመስተንግዶ አገልግሎት፣ የመኪና ኪራይ አገልግሎት፣ የህትመት አገልግሎት፣ የዲኮር ሞንታርቦና ጄኔሬተር አገልግሎት እንዲሁም የድንኳን አገልግሎት በግልፅ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሠራት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶችም ሆነ ግለሰቦች የሚከተሉትን መስፈርቶች በሟሟላት መወዳደር ይችላሉ።
1ኛ. በዘርፉ የንግድ ሥራ የተሰማሩ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው እና በመንግሥት የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ መሆን ይኖርበታል።
2ኛ. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
3ኛ. የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችሉ።
4ኛ. የመወዳደሪያ ዋጋው ቫትን ጨምሮ በግልፅ መፃፍ አለበት።
5ኛ. የሚያስገቡትን የጨረታ ሰነድ ማህተም ማድረግ፤ መፈረም እና አለመሰረዝ ይኖርበታል።
6ኛ. ተጫራቾች የጨረታው መመሪያ፤ የዕቃና አገልግሎት እስፔስፊኬሽን አጠቃሎ የያዘ የጨረታ ሰነድ በአካል መተው የማይመለስ በየሎቱ 200.00 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በወ/09/ፋ/ፅ/ቤት ሦስተኛ ፎቅ በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
7ኛ ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ በየሎቱ ተመላሽ የሚሆን የእቃዎች ዝርዝር
- ሎት 1 እስቴሽነሪ እቃዎች 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር ብቻ)
- ሎት 2 የፅዳት እቃዎች 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺ ብር ብቻ)
- ሎት 3 የደንብ ልብስ 15000.00 (አስራ አምስት ሺ ብር ብቻ)
- ሎት 4 የመኪና ጎማ እና የመኪና እቃዎች 7,000.00 (ሰባት ሺ ብር ብቻ)
- ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 15,000.00 (አስራ አምስት ሺ ብር ብቻ)
- ሎት 6 የፈርኒቸር እቃዎች 15,000.00 (አስራ አምስት ሺ ብር ብቻ)
- ሎት 7 የመስተንግዶ አገልግሎት 10,000.00 (አስር ሺ ብር ብቻ)
- ሎት 8 የመኪና አገልግሎት 10,000.00 (አስር ሺ ብር ብቻ)
- ሎት 9 የኅትመት አገልግሎት 10,000.00 (አስር ሺ ብር ብቻ)
- ሎት 10 የዲኮር፤ ሞንታርቦና ጄኔሬተር አገልግሎት 10,000.00 (አስር ሺ ብር ብቻ)
- ሎት 11 ድንኳን አገልግሎት 10,000.00( አስር ሺ ብር ብቻ)
8ኛ. ተጫራቾት የሚያቀርቡትን ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት።
9ኛ. የፎቶ ኮፒ ቀለምና የፕሪንተር ቀለም የሚያቀርቡ የ1 (አንድ) ዓመት ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
10ኛ.የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የሚያቀርቡ የ2 (ሁለት) ዓመት ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
11ኛ, ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ የቀረበውን የመወዳደሪያ ሀሳብ መቀየር፤ ማሻሻል ወይም ከጨረታ መውጣት አይቻልም።
12ኛ. የጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ ሆነ ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ወቅት ያሸነፈበትን የሽያጭ ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ከባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት።
13ኛ. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ጥራቱን የጠበቀ ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም ተጫራቾች ለሁሉም ምድቦች ናሙና ሲያቀርቡ ከ1 (አንድ) በላይ ማቅረብ አይቻልም።
14ኛ. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡30 በመሥሪያ ቤቱ ወጣት ማዕከል 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል፡፡ በዓል ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል።
15ኛ. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ጨረታውን ተወዳድሮ ያሸነፈ ድርጅት የተወዳደረባቸውን እቃዎች የእቃ ዋጋ ገበያ ላይ ጨመረ እቃው ከገበያ ላይ ጠፋ የሚል ሰበብ ተቀባይነት አይኖረውም።
ተጨማሪ መረጃና ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 011-8-93-30 66 ወይም በ011-8-93-31-99 ይደውሉ።
በየካ ክ/ከተማ የወረዳ 9 ፋይናንስ ፅ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-30
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-07-30 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Yeka Sub City Woreda 09 FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር በየሎቱ
- Published: Jul 18, 2026
- Posted at: 2026-07-18T07:35:18.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.