የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት እነ ትሁኔ በላይ እና በፍ/ባለዕዳ እነ አላረው እንግዳ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/235754 በ29/7/2018ዓ/ም እና በዋለውችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ፍርድ ያረፈበት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቤት ቁጥር 219 የመለያ ቁጥር 11/06/5167/102/01 የተመዘገበ የቦታ ካርታ ያለው የቦታው ስፋት 600 ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 24,865,600 (ሃያ አራት ሚሊዮን ስምንት መቶ ስልሳ አምስት ሺህ ስድስት መቶ) ብር ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆነ ታውቆ ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-18
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Jul 18, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.