ፐብሊክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት የደንብ አልባሳት፣ የፅዳት እቃዎች እና የጽሕፈት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም

ፐብሊክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችና አገልግሎቶችን መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና መሸጥ ይፈልጋል።

  • ሎት 1 የደንብ አልባሳት ፤
  • ሎት 2 የፅዳት እቃዎች
  • ሎት 3 የጽሕፈት እቃዎች፤

1. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር የሥራ ቀናት ከሎት 1 እስከ ሎት 3 ለእያንዳንዱ ሎት 500 በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 በአካል በመምጣት መግዛት ይችላሉ።

2. ከሎት 1 እስከ ሎት 3 ተጫራቾች በዘርፉ ንግድ ምዝገባና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የብቃት ማረጋገጫ እና የአቅራቢዎች የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆነ እና የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) ያለቸው፤ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ከሎት 1 እስከ ሎት 3 ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የሚያቀርቡትን የጨረታ ሠነድ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ ዋና እና ኮፒ በሁለት ፖስታ በማዘጋጀትና በኤንቨሎፕ በማሸግ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ኃላፊነት በተሰጠው አካል ተፈርሞበት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

4. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ 2% ሲፒኦ /Bid Bond/ ወይም በባንክ የተመሰከረለት በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 3 ለእያንዳንዱ ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው።

6. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻው ቀን የዕረፍት ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይከፈታል።

7. አገልግሎታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከሜክሲኮ ወደ ልደታ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡- ስልክ-011-50-4564

ፐብሊክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-03
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-03 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Public Service Transport Service
  • Bid bond: 2% ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published: Jul 20, 2026
  • Posted at: 2026-07-21T07:37:05.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders