ስፋቱ 330 ካ.ሜ የሆነ የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍርድ ባለመብት ዓባይ ባንክ እና በፍርድ ባለእዳ እነ ሳልጋይ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር መካከል ስላለው አፈፃፀም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 326203 በቀን 11/08/2014 ዓ.ም . በመ/ቁ.284984 በቀን 23/10/2017ዓ.ም በመ/ቁ.284984 በ 11/06/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ በ3ኛ የፍ/ባእዳ ተመዝግቦ የሚገኘው ቤት ቦሌ ክ/ከተማ በካርታ ቁጥር ቦሌ15/186/1127/00 ሴሪ ቁጥር 139550 የሆነው ስፋቱ 330ካ.ሜ የሆነ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ 18,436,620 (አስራ ስምንት ሚሊየን አራት መቶ ሰላሳ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ሀያ ብር) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 13 ቀን 2018ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የተረበ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት የሆነው ግለሰብ አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-19
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-08-19 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Jul 20, 2026
- Posted at: 2026-07-21T08:05:45.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.